• May 20, 2024

4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ

ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ!

የጋብርኤል ማርቲኔሊ – የእግር ኳስ ህይወት ከደቡብ አሜሪካ እስከ ሰሜን ለንደን

ByLeo Simera

Jun 5, 2023

ብራዚላዊው ኢንተርናሽናል ገና የ14 አመት ታዳጊ ሆኖ ነበር በስፖርቱ ስሙ መጠራት የጀመረው ። ጋቢ ያደገው የቤተሰቡ መገኛ በሆነው የሳኦፖሎ ከተማ ነው፤ አብዛኛውን የህይወት ክፍል ያሳለፈው ከከተማዋ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው ዩቱዋ ከተማ ነው፤ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ ግን ክለቦችን ቀያይሯል፤ በሀገሪቱ ታላቁ የሆነው እና ለሰባት ጊዜ የናሽናል ሊጉ አሸናፊ የሆነውን ኮረንቲያንስን የለቀቀበትን ጨምሮ ነው፤ የግራ ክንፍ ተጨዋቹ በመጀመሪያ የህይወት ክፍሉ ብዙ ፈተናዎኝ እንዳለፈ ይናገራል፤ በተለይም የቀደመ ህይወቱን መተው ፈታኝ ነበር፤ ነገር ግን ቤተሰቦቹን ለመርዳት ትልቁን ውሣኔ ማሳለፍ ነበረበት፤ ከትውልድ ቦታው ከወጣ በኋላ በለንደን የአራት አመታት ቆይታ አድርጓል፤ ቤተሰቡን መርዳት ደግሞ ትልቁ ስራው ነው፡፡

“ስለ እግር ኳስ ተጨዋቾች ሲወራ ሁልጊዜም ወደ አዕምሮዬ የሚመጣው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ነው፤ ልጅ እያለው እሱን መመልከት በጣም ያዝናናኛል፤ የጨዋታ ስታይሉን በጣም እወደዋለው፤ የህይወት መነሻዎቼ ቤተሰቦቼ ናቸው፤ ከልጅነት እድሜዬ አሁን እስካለሁበት ደረጃ ድረስ ከጎኔ ናቸው፤ በብዙ መንገድ ሲረዱኝ ነበር፤ ከመጀመሪያዎቹ ቀን አንስቶ ከጎኔ ናቸው፤ ድጋፍ ያደርጉልኛል፤ ምክር በመስጠት ሊረዱኝ ጥረት ያደርጋሉ፤ ወላጅ አባቴ ወጣት በነበረበት ወቅት እግር ኳስን ይጫወት ነበር፤ የሚጫወተው ግን ራሱን ለማዝናናት ነበር፡፡

“ልጅ እያለው እግር ኳስን መጫወት ያስደስተኝ ነበር፤ ወላጆቼ ደግሞ ያበረታቱኛል። እንደማስበው ቤተሰቦቼ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጨዋቾች ልጅ እንዲኖራቸው ህልሙ ነበራቸው፤ወላጆቼ ሁልጊዜም ያበረታቱኛል፤ ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ እግር ኳስ ተጨዋች ሆኜ እንዳድግ ይፈለጉ ነበር፤ እኔን ለመርዳት የሚችሉትን ነገር በሙሉ አድርገዋል፤ ህልም እና ጎሎቼን እንዳሳካ እገዛ አድርገውልኛል፡፡

ይህ ህልሙ ገና በታዳጊነት እድሜው በትክክለኛው ጎዳና መጓዝ ጀምሯል፤ የስድስት አመት ታዳጊ እያለ የሀገሩን ክለብ ኮረንቲያንስ ተቀላቀለ። ወላጆቹ በእግር ኳስ ህይወቱ ጅማሮ ላይ ድጋፋቸውን አድርገውለታል። በተለይም እናቱ የነበራት አስተዋፅኦ የላቀ ነው፤ “አባቴ ሁልጊዜም በስራ ላይ ነበር፤ እናቴ ከትምህርት ቤት ወደ ልምምድ ሜዳ ትወስደኛለች፤ ፉትሳል እጫወት ነበር፤ ከዚያ ደግሞ በትልልቅ ሜዳዎች ልምምዴን አደርጋለው፤ ከሰዓት በኋላ ልምምድ አደርግ እና ምሽት ላይ ደግሞ ፉትሳል እጫወታለው፡፡

“እናቴ ቀኑን በሙሉ ከእኔ ጋር ጊዜያዋን ታጠፋለች፤ አባቴ ስራውን ምሽት ላይ ጨርሶ መጥቶ ይወስደናል። እናቴ ማሽከርከር አትችልም ስለዚህም በባስ ወደ ቤታችን ለመጓዝ እስከ አንድ ሰዓት ተኩል ይወስድብን ነበር፤ ትምህርት ቤት እንገናኝ እና ወደ ባስ መጠበቂያው እንጓዛለን ባሱ ሁልጊዜም የሚጥለን በተመሳሳይ ቦታ ነው፤ ከዚያ እስከ ልምምድ ቦታው የ10 ደቂቃ ጉዞ እናደርጋለን፤ ለአራት አመታት በዚህ መልኩ ቀጥለናል፤ ከ10-14 እስካለው እድሜዬ በኮረንቲያስ የነበረኝ ቆይታ እንደዚህ ያለ ነበር፡፡

“ለኮረንቲያንስ መጫወት የጀመርኩት ገና የስድስት አመት ታዳጊ ልጅ ሆኜ ነው፤ በዚያ እድሜ በተለመደው የሜዳ ክፍል ስፋት አትጫወትም። ስለዚህም በመጀመሪያዎቹ አመታት የፉትሳል ጨዋታ ታደርጋለህ ከዚያም የሜዳ ላይ ጨዋታዎችን ጀመርኩ። እድሜዬ አስር ሲሆን ማለት ነው፤ ከ11 አመት በታች ቡድን ውሰጥ መጫወትም ነበር፤ ፉትሳል በአምስት ተጨዋቾች መካከል የሚደረግ የቤት ውሰጥ ጨዋታ ነው፤ በብራዚል የተለመደ ነገር ነው፤ ጋቢ ጎል የማስቆጠር አፕታይቱን የከፈተውም በዚያን ወቅት ነው፡፡

“ሁልጊዜም የማጥቃት ቦታ ላይ መጫወት ያስደስተኝ ነበር፤ እግር ኳስን ከጀመርኩበት ወቅት አንስቶ ማለት ነው፤ እስከ ዘጠኝ አመቴ ድረስ በፉትሳል ሜዳ ተጫውቻለው፤ ስለ ጎል ማስቆጠር ሪከርዱ ሲጠይቅ ደግሞ ጥሩ የሚባል እንደነበር ያስታውቃል፤ ብዙም ሳይቆይ የጋቢ አባት አዲስ ስራ አገኙ፤ ከትልቁ ሳኦፖሎ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የኢትዩ ከተማ ማለት ነው። ከተማዋ የብዙ ቱሪስቶችን ቀልብ በመሳብ የምትታወቅ ናት፤ ለጋቢ ክለብ የመቀየር ነገር እርግጥ ሆኖ ኢቱያኖ የተባለውንም ክለብ ተቀላቀለ፤ ቡድኑ የሚጫወተው በብራዚል የሀገር ውሰጥ እግር ኳስ በሁለተኛው ዲቪዚዮን ነው፤ ጋቢ ሲደርስ ደግሞ ኢቱያኖ ከቶፕ ሶስት ዲቪዚዮን ውጭ ሆኖ ነበር፡፡

አባቴ አዲስ ስራን አገኘ ።ከዚያም ከከተማ ውጭ መውጣታችን እርግጥ ሆነ፤ የሁለት ሰዓት የመኪና መንገድ ያለው ነው፤ የእኔም ህይወት በብዙ መልኩ ሊለወጥ ግድ አለው፤ ለኮረንቲያንስ ስትጫወት ትልቅ ክለብ እንደሆነ በሚገባ ታውቃለህ፤ ሁልጊዜም አሸናፊ የሆነ ቡድን ነው፤ ወደ ኢቱያኖ ሳመራ እያንዳንዱን ጨዋታ እንሸነፍ ነበር፤ ይህ ደግሞ ለእኔ በጣም አስቸጋሪ ነበር። እሱን ነገር አልወደዱኩትም፤ ወደ ኮረንቲያንስ ከተመለስኩ ሁለት ነገር ይቀላል። በሳኦፖሎ ሁሉም ጓደኞቼ አሉ፤ ከህይወቴ ሰባት እና ስምንት አመታትን ያሳለፍንበት ነው። ወደ አዲስ ክለብ ማምራቴ ፈታኝ ነበር፤ ማንንም ሰው አላውቅም ነበር ። እግር ኳስን መጫወት እፈልጋለው፤ በቤተሰቦቼ ምክንያት መጓዝ ነበረብኝ አባቴ አዲስ ስራ አግኝቷል፤ እናም እግር ኳስን እየተጫወትኩ መቀጠል እፈልግ ነበር፡፡

ሜዳ ሲገባ ትኩረቱ በሙሉ የእግር ኳስ እድገቱን ማስቀጠሉ ላይ ነበር፤ በቶሎ ከቡድኑ ጋር መዋሀድ እንደሚችልም ተማምኗል፤ አዲስ የቡድን አጋሮቹ የተቀበሉት በተለየ መንገድ ነው፤ ምክንያቱም የመጣው ከትልቅ ክለብ ነው፤ “እንደ እሱ አይደለም ምክንያቱም በዚያ እድሜ ማንም ሰው አያውቀኝም 14 አመቴ ነበር፤ ልክ እንደ ጥሩ ተጨዋች ተመልክተውኝ ይሆናል፡፡ ለእነሱ ተስማሚ እንደሆንኩ ማለት ነው፤” የቡድን አጋሮቹ የተመለከቱት ትልቅ አቅም እንዳለው ተጨዋች ነው፤ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ወደ አውሮፓ ማቅናቱ እርግጥ ነበር፡፡

“አዎ በ13 ወይም በ14 አመቴ ለሙከራ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ማንቺስተር አምርቼያለው ። በእርግጠኝነት ግን ጊዜው ገና እንደነበር አልዘነጋሁም። አሁንም ገና ወጣት ነኝ፤ ስለዚህ ማንም አያውቀኝም፤ ለእኔ አዲስ ልምድ ነው። በቂ መንገድ ተጉዣያለው፤ መጀመሪያ አካባቢ አልወደድኩትም ነበር፤ በቤቴ መሆን እፈልግ ነበር፤ ከአባቴ ጋር ወደ አዲስ ቦታ መጓዜ አስፈርቶኛል የተለየ ሀገር ነው፤ የተለየ ቋንቋ መናገር አልችልም ለእኔ ከባድ ነበር፡፡ “

ብራዚልን መልሶ አገኛት በድጋሚ ዝናውን መገንባት ጀመረ ለኢቱያኖ ለመጀመሪያ ቡድን ጨዋታውን ያደረገው በ16 አመቱ ነው፤ በቶሎ በቋሚነት በመጫወት በሀገር ውስጥ የፉክክር ጨዋታ ጎል ማስቆጠር ጀመርኩ ። የ18ኛ አመቱ በ2019 የሰኔ ወር ሲያከበር በኋላ ወደ አርሰናል አመራ የቀድሞ የሙከራ ጊዜያቶች ብዙ ነገር አስተምረውት ነበር፤ ስለዚህም በባህር ማዶ ለአዲስ ፈተና ራሱን አዘጋጀ፡፡

“ምናልባትም የሙከራ ጊዜያቶቹ ሳያግዙኝ አይቀሩም እርግጠኛ ግን አይደለውም፤ በአዕምሮዬ የነበረው ነገር አርሰናልን ለመቀላቀል ዝግጁ ነበርኩ፤ መጠነኛ ጥርጣሬዎች ነርሩ፤ ገና ወጣት ነበርኩ፤ ቋንቋውን መናገር አልችልም፤ ነገር ግን እሱ ችግር አልነበረም፤ ምክንያቱም በአዕእምሮ በኩል ዝግጁ ነበርኩ፤ በራስ መተማመኔ ከጅምሩ ከፍ ያለ ነበር፤ ቤተሰቤ በጣም ደስተኞች ነበሩ፤ በተለይ እናቴ በጣም ረጅም ጉዞ አድርጋለች፤ አዲስሀገር ነው ነገር ግን ተጨንቀለች፤ ታውቃለህ፤ በጣም ትሁት መሆን ነበረብን፤ እንዴት ማስረዳት እንዳለብኝ አላውቅም፤ እንደ ቤተሰብ ለእኛ ሁሉም ነገር አዲስ ነው ለእኛ አዲስ ምዕራፍ ነው፤ እንዴት ሊሰራ እንደሚችል አናውቅም፡፡

እንደ ሳኦፖሎ ባለ ትልቅ ከተማ መኖሬ በእጅጉ አግዞኛል፤ ከኢቱዩኖ ወደ ለንደን ተሸጋግረናል፤ ያደኩት በሳኦፖሎ ከተማ ነው፤ በለንደን ለመኖር ግን ዝግጁ ነበርኩ፡፡

“ለአርሰናል ፊርማዬን ማኖሬን ሲያውቁ ቤተሰቦቼ በሙሉ በጩኸት ደስታቸውን ገልፀዋል፤ እኔም በተመሳሳይ ደስተኛ ነበርኩ፤ ቤተሰቦቼ ከጅማሮ አንስቶ ከእኔ ጋር ሲንቀሳቀሱ ነበር፤ ለስምንት እና ዘጠኝ ወራት እስክላመደ ድረስ ከጎኔ ነበሩ፤ በቆይታዬ ተላምጄ አዲስ ቤት እስካገኝ አብረውኝ ነበሩ። ስለ ህይወቱ ብዙ የማውቀው ነገር አልነበረም፤ ስለዚህም ከጎኔ ሆነው እንዲያግዙኝ እፈልግ ነበር፤ እነሱ የህይወቴ አስፈላጊው ክፍል ናቸው፡፡

በለንደን የነበሩኝ የመጀመሪያ ወራት ለእኔ በጣም አስቸጋሪ ነበርን ከኢቱያኖ ወደ ኮረንቲያንስ ያደረኩት ጉዞ ለእኔ ትልቅ ለውጥ ነበር፤ ከኢቱያኖ ወደ አርሰናል ዳግም እጅግ ትልቅ ለውጥ ሊባል የሚችል ነው፤ የመጫወት እድል ያገኘሁት ከአለማችን ምርጥ ክለቦች መካከል በአንዱ ነው፤ በጣም ደስተኛ ብሆንም በተመሳሳይ ተረብሼ እንደነበር ግን ለመሸሸግ አልፈልግም። ለመጀመሪያ ጊዜ የተመለከትኳቸው ሰዎች አባ ሜሱት እና ላካን የመሳሰሉ ተጨዋቾች ናቸው፤ ይህ ለእኔ አስደናቂ ሊባል የሚችል ነው፤ ሁሉም ታላላቅ ሊባሉ የሚችሉ እግር ኳሰኞች ናቸው፤ ለእኔ በጣም ጥሩ ነገር ነው፤ እነዚህ ሁሉ ተጨዋቾች ወደ አዚህ ክለብ ከመጣው በኋላ ትልቅ እገዛን አድርገውልኛል፡፡

“ስለ እውነት ለመናገር የመጀመሪያ የልምምድ ክፍለ ጊዜዬ ድካሙ ከፍ ያለ ነበር፤ የቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት እንደነበር አስታውሳለው ። ይበልጥ ትኩረት የሚያደርገው ደግሞ በሩጫ እና አካል ብቃት ላይ ነው፤ በጣም ከባድ የሚባል አልነበረም፤ የትኛውም ተጨዋች እግር ኳስን ከመጫወቱ በፊት ሊያደርጓቸው የሚገባው ነገሮች ናቸው፡፡

“በመጀመሪያ ወደ ልምምድ ስገባ ትንሽ እንግዳ ነበር፤ በቅድመ ውደድር ዘመን ዝግጅት ወደ አሜሪካ አቅንተን ነበር፤ ይበልጥ ነፃነት እንዲሰማኝ ሆኛለው ጋቢ በመጀመሪያ ጨዋታው በወዳጅነት ግጥሚያ የሰሜን ለንደኑ ክለብ ኮሎራዶ ራፒድስ 3ለ0 ሲያሸንፍ ኳስ እና መረብን ማገናኘት ቻለ፡፡ በ2019/20 የውድደር ዘመን በዋናው ቡድን ውሰጥ መጫወት የሚችልበትን እድል አገኘ፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የሀገሩ ሰው የሆነው ኤዱ የክለቡ ቴክኒካል ዳይሬክተር በመሆን ተሾመ። ማርቲኔሊን በኮረንቲያንስ በቴክኒካል ዳይሬክተርነት ሲሰራ ታዳጊ እድሜ ላይ እያለ በሚገባ ያውቀው እንደነበር ይታወሳል፡፡

“ከኤዱ ጋር ገንቢ የሆነ ንግግር ማድረጌን አስታውሳለው በብሔራዊ ቡድን ውስጥ ነበርኩ፤ በ2019 በኮፓ አሜሪካ ስብስብ ውስጥ መካተት ችዬ ነበር፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ በአርሰናል ቤት ዳግም መገናኘት ቻልን፡፡ ጋቢ አርሰናልን ከተቀላቀለ አራት አመታት ተቆጥረዋል፤ በቆይታው በ127 የዋናው ቡድን ጨዋታዎች 33 ጎሎችን ከመረብ ማገናኘት ችሏል። ሜዳ ላይ ራሱን በሚገባ ዘና ለማድረግ ጥረት ያደርጋል፡፡

እናቱ አሁንም ከጎኑ ሆነ እንደምታደግፈው ያስታውቃል፤ “እድሜዬ ወደ 22 እየተዘጋ መሆኑን የዘነጋች ይመስለኛል፤ አሁንም የስምንት እድሜ ላይ እንደምገኝ ታስባለች። ነገር ግን ይህ የተለመደ ነገር ነው፤ ሁሉም እናቶች ልክ እንደዚህ ናቸው፤ “አሁን ላይ ጋቢ በአርሰናል ደጋፊዎች ልብ ውስጥ መግባት ችሏል፤ ከእነሱን ለረጅም ጊዜ እያገለገለ እንደሚቀጥልም ትልቅ ተስፋን ሰንቀዋል፡፡

በሀትሪክ ስፖርት ፀሐፊ ሳምሶን አበበ ተዘጋጅቶ በ 4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ የቀረበLeave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *