• May 19, 2024

4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ

ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ!

ሙጂብ ቃሲም ቀጣይ አመት በሀዋሳ ይቆይ ይሆን …?

ByLeo Simera

Jun 6, 2023

በእግር ኳስ ህይወቱ ሁለተኛ ክለቡ ወደ ሆነው ሀዋሳ ከተማ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ፋሲል ከነማን በመልቀቅ ለሁለት አመት በከፍተኛ ገንዘብ የፈረመው አጥቂው ሙጂብ ቃሲም ከሀዋሳ ጋር በቀጣይ አመት የሚያቆየው ውል ቢኖረውም የአንድ አመቱን ገንዘብ መልሶ ተስማምቶ በመልቀቂያ ደብዳቤ ሊለቅ የሚችልበት እድል መኖሩን ኢትዮ ፉት ስፖርት አጣርታለች። ለመልቀቁ ውሳኔ ከጫና ጋር ይያያዛል ተብሏል።

ሙጂብ ከዚህ በፊት በሲዳማ ቡና በአማካይ ተከላካይነት መጫወት ከጀመረ በኃላ ለሀዋሳ በተከላካይነት በአዳማ በተከላካይ እና አጥቂነት በፋሲልም በተከላካይ እና አጥቂነት ከዚህ በፊት ያገለገለ ሲሆን ዘንድሮ ወደ ሀዋሳ ከተመለሰ በኃላ ደግሞ በአጥቂ ቦታ እየተጫወተ ይገኛል።

ተጫዋቹ ቀጣይ አመት በሀዋሳ ይቀጥላል ? አልያ አይቀጥልም ? በቅርቡ ምላሽ ይጠበቃል።

ለሚወስዱት መረጃ ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *