• May 20, 2024

4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ

ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ!

ሳምንቱን በስፖርት

ByLeo Simera

Jun 18, 2023

👉 ሪዮ ፈርዲናንድ ” ማንችስተር ዩናይትድ በኳታር ባለሀብት መያዙ የማይቀር ጉዳይ ነው። ክለቡን መግዛታቸውን በጥቂት ቀናት ውስጥ ይፋ ይደርጋል” ብሏል

👉 ማንቸስተር ዩናይትድ በኳታሩ ሼህ ጃሲም ቢን ሀማድ አል ታኒ ለሚመራው የባለሀብቶች ቡድን ራሱን ከ6 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ዋጋ ለመሸጥ እየተደራደረ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።

👉ሊዮኔል ሜሲ በቀጣዩ የአለም ዋንጫ እንደማይሳተፍ አሳውቋል

👉ኪሊያን ምባፔ ከፒኤስጂ ጋር ስለ ኮንትራት ማራዘሚያ በጭራሽ አልተነጋገርንም። ብሏል ተጫዋቹ አክሎም ሊዮኔል ሜሲ በፓሪሱ ክለብ ተገቢውን ክብር እንዳላገኝ ተናግሯል

👉አርሰናል ካይ ሃቨርትዝን ከቼልሲ እንዲሁም ዴክላን ራይስን ከዌስትሃም ለማስፈረም ተቃርቧል።

👉ማርክ-አንድሬ ቴር ስቴገን የስፔን ላሊጋ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል!🧤🇩🇪

👉ማንችስተር ዩናይትድ ለጃዶን ሳንቾ 60 ሚሊዮን ፓውንድ የሚያቀርብ ክለብ ካለ ተጨዋቹን ለመሸጥ ዝግጁ ነው ሲል ስካይ ስፖርት ዘግቧል

👉በ 2023/24 የሚደረጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ  የውድድር ዓመት ሁሉም ጨዋታዎች ይፋ ተደርጎዋል…ሙሉ ፕሮግራሙን በቴሌግራም ቻናላችን ተለቆዋል ገብቶ ይመልከቱ

👉ሮድሪ የ2022/23 የቻምፒየንስ ሊጉ ምርጥ ተጫዋች በመባል ተመርጧል!

👉ፔፕ ጋርዲዮላ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ካነሳ ቡሃላ “ሪያል ማድሪዶች ተጠንቀቁ እናንተ ላይ ለመድረስ 13 ዋንጫዎች ቀርቶውናል። እኛ በመንገዳችን ላይ ነን ትንሽ ብትተኙ እንደርስባቹዋለን።”

👉አርሰናል ኒኮላስ ፔፔን ለመሸጥ 10 ሚሊዮን ፓወንድ ዋጋ ለጥፈውበታል መድፈኞቹ ከዚህን በፊት ተጫዋቹን በ 75 ሚሊዮን ፓውንድ መግዛታቸው አይዘነጋም።

👉ሪያል ማድሪድ ጁዴ ቤሊንግሀምን በይፋ አስፈርሟል ተጫዋቹ በማድሪድ ቤት 5 ቁጥር ማሊያን በማጥለቅ ይጫወታል።

👉አዲሱ የአል ኢቲፋቅ አሰልጣኝ በመባል የተሾመው ስቴቨን ጄራርድ ፊሊፔ ኩቲንሆ እና ሳዲዮ ማኔን ማስፈረም ይፈልጋል። 🇸🇦(Tutto mercato)

👉ዚንቼንኮ “ሁሉም የሩሲያ እና የቤላሩስ አትሌቶች ከስፖርቱ አለም መታገድ አለባቸው!”

👉ሪቻርሊሰን” ሪያል ማድሪድ የዓለማችን ትልቁ ክለብ ነው እናም እያንዳንዱ ተጫዋች ማሊያውን መልበስ ይፈልጋል ።”

👉ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በሳኡዲ አረቢያ ነገሮች ከባድ እንደነበሩ እና አሁን ሁሉንም መላመዱን ተናግሯል።

👉ሜሲ በእግር ኳስ ህይወቱ ፈጣኗን ጎል በዚህ ሳምንት አውስትራሊያ ላይ አስቆጥሯል።

👉ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴሂያ ከ12 ዓመታት የማንችስተር ዩናይትድ ቆይታ በኋላ በክረምቱ እንደሚለቅ ሚረር ስፖርት በድረገፁ አስነብቧል።

👉”አርሰናሎች መጀመሪያ ላይ ማሰን ማውንትን ለማስፈረም ኢላማ አድርጎ የነበር ሲሆን የማውንት ምርጫ ማንችስተር ዩናይትድን መቀላቀል እንደሆነ ሲያውቁ ነው ፊታቸውን ወደ ካይ ሀቫርትዝ ያዞረው”David Ornstein

👉ሞይስ ካይሴዶ ቼልሲን ለመቀላቀል ወስኗል። ብራይተኖች ሞይስ ካይሴዶን ለመሸጥ ከ93 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ይፈልጋሉ ! 🇪🇨 (TeleFootball)

👉የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ውጪ ሆኗል.. በዚህ ሳምንትም ከአርባምንች ከተማ ጋር ያደረጉትን የወዳጅነት ጨዋታ 1 ለ 0 ተሸንፏል!

👉ለሜቻ ግርማ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታሪክ አዲስ ታሪክ ፅፏል። በትዉልድ ኬኒያዊ በነበረዉ አትሌት ለ2 አስርት አመታት ተይዞ የነበረዉን የአለም ክብረ ወሰን(7:53.63) ለሜቻ ግርማ በ7:52.11 አሻሽሎታል።

👉በኖርዌይ ኦስሎ በተደረገው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያዊው ዮሚፍ ቀጄልቻ በአምስት ሺህ ሜትር አሸንፏል። ዮሚፍ ከኡጋንዳዊው ኪሊሞ ጋር ተናንቆ በሰከንዶች ልዩነት በማሸነፉ ትልቅ አድናቆትም ተችሮታል።

በድምፅ ለማዳመጥ 👇

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *