• May 19, 2024

4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ

ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ!

የእለተ ረቡዕ ሰኔ 14/2015ዓ.ም የዝውውር ዜናዎች

ByLeo Simera

Jun 21, 2023

👉መድፈኞቹ የቼልሲውን ካይ ሀቨርትዝን ዝውውር ማጠናቀቃቸው ተሰምቷል። ተጫዋቹ በበርካታ ክለቦች እየተፈለገ ቢሆንም ማረፊያው እዚያው ሎንዶን ሆኗል። አርሰናል ለጀርመናዊው አጥቂ 65 ሚሊየን ፓውንድ ከፍሏል።

👉ቶማስ ፓርቴ ከአርሰናል ጋር ሊለያይ ስለመሆኑ ተዘግቧል።ስለሚለቅበት ሁኔታም ወኪሉ ከክለቡ ጋር እየተነጋገረ ይገኛል። በአርሰናል እስከ 2025 ድረስ የሚያቆይ የውል ስምምነት አለው።ቶማስ ቀጣይ ማረፊያውም የሳዑድ አረቢያ ሊግ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።

👉አርሰናል እና አያክስ አሁን የቲምበርን ዝውውር ለመጨረስ ከስምምነት እንደሚደርሱ ይጠበቃል።(Mike verweij 🥈)

👉ጁሪየን ቲምበር ትኩረቱን ያደረገው ወደ አርሰናል ዝውውር ላይ ብቻ ነው። ባየር ሙኒክ ለእሱ ጥያቄ ቢያቀርብ እንኳ እሱ ወደ ባየርን የመሄድ ፍላጎቱ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይገባል። [#MikeVerweij]

👉የሶስትዮሹ ዋንጫ ባለድል ማንቸስተር ሲቲ ማቲዮ ኮቫቺችን ለማስፈረም ተቃርቧል። ለዝውውሩም ከ25 እስከ 30 ሚሊየን ፓውንድ እንደመደበም ታውቋል። እንዲሁም የ RB ላይብዢጉን ክሮኤሺያዊውን ተጫዋች ግቫርዲዮልን ለማዘዋወር በግላዊ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውም ታውቋል።

👉የማንቸስተር ሲቲው ተጫዋች ካይል ዎከር ከክለቡ ሊለቁ ከሚችሉ ተጫዋቾች መካከል አንደኛው እንደሆነ ሲገለፅ ነበር፣ እናም ይህን ተጫዋች የቡንደስሊጋው ሻምፒዮን ባየርሙኒክ ካይል ዎከርን ለማስፈረም ተቃርቧል።

👉በማንቸስተር ዩናይትድ የአምስት ዓመታት ቆይታ ያለው ፍሬድን ክለቡ ለመሸጥ ተዘጋጅቷል።የ30 ዓመቱን ተጫዋች ለመግዛት ፉልሀም ተዘጋጅቷል፣ ማንቸስተር ዩናይትድ ለዝውውሩ 20 ሚሊየን ፓውንድ እንዲከፈለው ይፈልጋል።

👉ክፍተቶች ቢኖሩም ማንቸስተር ዩናይትድ የአንድሬ ኦናናን ዝውውር ስምምነትን ለማጥበብ እና ተጫዋቹን ለማስፈረም ይሞክራል ፤ ማን ዩናይትድ ለዝውውሩ €40 ሚሊዮን ለማቅረብ እያሰቡ ሲሆን ኢንተር ቢያንስ ተጨማሪ €10 ሚሊዮን ዩሮ ይፈልጋል።( ጋዜጣ ዴሎ ስፖርት )

👉ማንቸስተር ዩናይትድ ሀሪ ማጓየር ወይም ስኮት ማክቶሚናይን የዝውውሩ አካል አድርጎ ዴክላን ራይስን ለማስፈረም ለዌስተሀም ጥያቄ ሊያቀርብ ነው።(JBurtTelegraph 🥈)

👉ቼልሲ የማንችስተር ዩናይትድን ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል።

👉የኢንተርሚላኑን ኒኮሎ ባሬላን ለማዘዋወር ጥብቅ ፍላጎት የነበራቸው ኒውካስትል ዩናይትዶች በዝውውሩ ላይ የነበራቸውን ፍላጎት ማንሳታቸው ተነግሯል።

👉የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስዠ የቀድሞው የሊቨርፑል አማካኝ ጆርጂኒዮ ዋይናልደምን መሸጥ ይፈልጋል።ይህ ተጫዋች ባለፈው ዓመት በውሰት ያሳለፈው ሮማ ነበር።

👉የክሪስታል ፓላሱ አንጋፋው አሰልጣኝ በክለቡ እንደሚቆዩ ማረጋገጫ ተሰጥቷቸዋል ከወራት በፊት በድጋሚ ቡድኑን ለማሰልጠን የተረከቡት አሰልጣኙ በቀጣይም በክለቡ ይቆያሉ ተብሏል።

👉ጀርመናዊው አማካኝ ቶኒ ክሩስ በሳንቲያጎ ቤርናቢዮ እስከ 2024 የሚያቆየውን ውል ፈረም።አዲሱ ስምምነቱ በማድሪድ ያለውን ቆይታ 10 አመታት ያደርሰዋል።

👉 ኢካይ ጉንዶሀን ለባርሴሎና የ ሁለት አመት ውል ለመፈረም መስማማቱን ከስፔን የሚወጡ መረጃዎች ጠቆሙ።

👉ባርሴሎና ሶፊያን አምራባትን ለማስፈረም ከሚደረገው ውድድር ወጥቷል።(ጄራርድ ሮሜሮ🥇)

👉ካንቴ አል ኢትሀድን ተቀላቅሏል ፤ 7 ቁጥር መለያንም ተረክቧል።

👉ሀኪም ዚዬሽ አልናስርን ለመቀላቀል በቃል ደረጃ ተስማምተዋል

👉ቼልሲዎች ኤድዋርድ ሜንዲን ለመሸጥ ከሳውዲው አል አህሊ ጋር ሙሉ የቃል ስምምነት ላይ ደርሰዋል

👉ሂዩንግ ሚን ሶን ወደ ሳውዲ አረቢያ የማቅናት ፍላጎት እንደሌለውና በቶተንሀም መቆየትን እንደሚፈልግ ተናግሯል።(Sky sport news)

👉አል ሂላል ካሊዱ ኩሊባሊን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል

👉አል ሂላል ለአልቫሮ ሞራታ ዝውውር £27M ለአትሌኮ ማድሪድ አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *