• May 18, 2024

4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ

ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ!

አፍሪካዊ ዝርያ ያለው የክርስቲያኖ ሮናልዶ ያልተነገሩ እውነታዎች

ByLeo Simera

Jul 4, 2023

የአለማችን ኮከብ እግር ኳስ ተጫዋች ስለሆነው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በተመለከተ ሲነሳ ብዙ ጊዜ የማይገለፀው የቅድመ አያቶቹ መገኛ ከአጉራችን አፍሪካ እንዴ ሚመዘዝ ሲግልፅ አይሰማም

ኬፕ ቨርዲ በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ደሴት ናት እናም ሮናልዶ በአባቱ በኩል ያሉ ቅድመ አያቶቹ ተወልዶ ያደጉት በዚች ምዕራባዊ አፍሪካ ደሴት ሲሆን ከብዙ አመታት በፊት የተሻለ ህይወት ፍለጋ ወደ ፖርቹጋል ተጓዙ

በዛም ህይወታቸውን ቀጥሎ ከአፍሪካዊነታቸው ይልቅ ፖርቹጋላዊነታቸው እየጎላ መጣ

ከደሃ ቤተሰብ ተወልዶ ዛሬ አለም ላይ ካሉ ቢሊኔር የእግር ኳስ ኮከብ መካከል አንዱ የሆነው ሮናልዶ በታዳጊነት ዘመኑ እጅግ የሚያሰለቸው በክፍል ውስጥ ተቀምጦ የሚያሳልፋቸው ግዜያቶች ናቸው

ለሱ አስደሳች ነገር ኳስ እና ኳስ ብቻ ነው በዚህም ውጤታማ በመሆኑ ገና የ 8 አመት ታዳጊ እያለ ፖርቹጋል ሊዝበን ውስጥ የሚገኝ ስፖርቲንግ CB የሚባል ዓይን ውስጥ ገባ ከዚያም ክለቡ ታዳጊውን ክርስቲያኖ ሮናልዶ የተውለደበትን ከተማ ለቆ ወደ ሊዝበን እንዲመጣ ጋበዘው

ሆኖም ይሄ ግብዥዓ ከቤተሰቡ ተለይቶ ለማያቀው ታዳጊ ትልቅ ውሳኔ የሚጠይቅ ጉዳይ ሆነ… ሮናልዶ ቤተሰቡ ካለበት የከፋ ደህነት ሊያወጣቸው የሚችልበት መልካም አጋጣሚ እንዳገኘ በማወቁ እያለቀሰ ቤተሰቡን ጥሎ ወደ ሊዝበን ተጓዘሙሉ ሀስቡን እና ችሎታውን በእግር ኳስ ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገው ሮናልዶ ውጤታማ ለመሆን በሚሞክርበት ጊዜ የልብ ታማሚ መሆኑን በሀምኪሞች ተገለፀለት ሆኖም ይሄ የልብ ህመሙ ብዙ ሳይቆይ ወደ ሙሉ ጤንነት ተመልሶ ዝነኛ ኳስ ተጫዋች የምሆን ጉዞውን ቀጠለ….

በቪዲዮ ለምትፈልጉ 👇👇

የክርስቲያኖ ሮናልዶ የፍቅር ታሪክ

በዓለም ካሉ ዝነኛ እግር ኳስ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከእግር ኳስ ስኬቱ ጎን ለጎን በፍቅር ህይወቱ ስኬታማ ነው

በእርግጥ ይሄንን በተመከተ ከብዙ ሴቶች ጋር የፍቅር ግኑኝነት መጀመሩን አስመልክቶ በተለያዩ ሚዲያዎች ስሙ ይነሳል…

ሆኖም በአንድ ወቅት አንድ ሚዲያ ስለ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የፍቅር ህይወት ሲፅፍ ይሄ ሰው ስኬታማ ነው

እንደሰው ደግሞ ማፍቀር ይፈልጋል በዚ አጋጣሚም ከአንድ ሴት ጋር ሊተዋወቅና እውነተኛ የፍቅር አጋሩን እስኪያገኝ ድረስም ከተለያዩ ሴቶች ጋር የፍቅር ህይወት ሊጀመር እና ሊያቆም ይችላል ይሄንን ጉዳይ እንደድክመት ልናይበት አይገባም ሲል ፅፏል

የዚህን ዝነኛ ኮከብ የፍቅር ህይወት አጥንተው የፃፉ ጋዜጠኞች ይሄን የሮናልዶ ግንኙነት በተመለከተ የሚያቃቸውን ሴቶች በሶስት ደረጃ ከፋፍሎ ይመድቡዋቸዋል በዚህም መሰረት

1ኛ የረጅም ጊዜ የያዛቸው እና በይፋ የታወቁ ግኑኝነቶች

2ተኛው ለተወሰነ ጊዜ ጀምሮ የተዋቸው ግኑኝነቶች

3ደግሞ.. ይፋዊ እውቅና የሌላቸው ሆኖም በተለያዩ ግዜያት የፍቅር ግኑኝነት ነበራቸው በሚል እንደሚከተለው አስቀምጦታል

በዚህም መሰረት ክርስቲያኖ ሮናልዶ ዝነኛ ከሆነ ቡሃላ በጓደኝነት ረዘም ላለ ጊዜ የያዛቸው የፍቅር ጓደኞች… ጆርዳና ጃርዴል… መርቼ ሮሚዮ…. ጌማ አክቲሰን…. ኔዳ ጋላዶ… አሪና ሻክ… ከነዚህ ጋር ከአንድ እስከ 5 አመት የሚሆን የፍቅር ግኑኝነት ነበረው

በሌላ በኩልም ከልጆቹ እናት ከሆነቺው እና ስብስባ ከያዘቺው ጆርጊና ጋር ከመገናኝቱ በፊት ለአጭር ግዜያት ከተለያዩ ሴቶች ጋር የፍቅር ግኑኝነት ነበረው ከነዚህም መካከል… ሚያ ጁድከን….ቢፓሻ ባሱ… ፋኤላ ፊኮ…. ፓሪስ ሂልተን… ኦልቪያ ሳንደርስ ሲሆኑ

የክርስቲያኖ ሮናልዶን የፍቅር ታሪክ በ3 ከፋፍሎ የመደቡት ፃፊያን በሶስተኛ ደረጃ የፃፉት ደግሞ ሮናልዶ ለአጭር ቀናት ፍቅር የተጋራቸውን ሴቶች በመዘርዘር ሲሆን እነዚህም… ኪምካርዳሽያ ጋር በ 2010.. አንድሳ ኡች 2013… ኤልስያ ዴ ፓኒሲስ… ዳኔላ አቻልቬስ… ኤልስያ ቴድች…. አሌግዛንደር አንቦስዮ… ክርስቲያን ቡቺኖ….ኤልስያ ሮቤች ካዜንደራ ዴቪስ… በተጨማሪም ሪታፔ ሌላ… ኦማል ሳቢ… ዲያና ሞራሌስ… ሜናሌ ታርቲንስ… ሉቺያ ቬላሎን… ኒኮሊታ ሎዛኖቫ… ድዚን ኮርዴ ከነዚህ ሴቶች ጋር በተለያየ ጊዜ ይፋዊ ግኑኝነት እንዳለው ዘግቧል

ይህ ሁሉ የሆነው አሁን የልጆቹ እናት ከሆነቺው ከጆርጊና ጋር የፍቅር ግኑኝነት ከመጀመሩ በፊት ነው

እነዚህ በአሁኑ ወቅት በምስሉ ላይ የሚታዩት ሴቶች በአሁኑ ወቅት አብዛኞቹ የፍቅር ህይወት የመሰረቱ ሲሆን በአንድ ወቅት የሚወዱትንና የሚወዳቸው ሰው ከሆነው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር በአሁኑ ጊዜ ምንም አይንት ግኑኘት የላቸውም

ስለዚህ ጉዳይ አስመልክቶ የፃፉት ሰዎች እደሚሉት ክርስቲያኖ ከተለያዩ ሴቶች ጋር የፍቅር ግኑኘት እንደመጀመሩ ተመሳሳይ የያዛት ሴት የለችም ይላሉ… ሁሌም ከአንድ ሴት ጋር ሲሆን አይኑን ይጨፍናል.. ወደ ሌላ ሴት የሚሄደውም የያዘው ግኑኝነት ስበላሽ ወይም ስለያዩ ነው ይላሉ

በሙያቸው አብዛኞቹ ሞዴሊስት… ጋዜጠኞች እና በተለያየ መስልክ እውቅና ያላቸው ሲሆኑ ከበዚህም ውስጥ አንዳቸውም ዝነኛ ያለሆነ አይገኝም

Maria Dolores ከባሏል እና ከልጆቿ ጋር በአንድ ጠባብ ቤት ውስጥ ትኖራለች የዚ ቤተሰብ የድህነታቸው  መጠን ከእጅ ወደ አፍ ከሚባለውም በታች ነው ይሄንን ድህነታቸውን ደግሞ ያከፋው የባሏ ጠጪ መሆን ነው ጆሴ ዴኒስ በየ ቀኑ ይጠጣል እናም በዚህ የደንነት ህይወት ውስጥ እያለች አለፍ አለፍ እያለ ህምመም ይሰማት ጀመር

ማሪያ ይሄንን ህመም ታውቀዋለች ይሄ አይነት ህመም ሚሰማትም ፅንስ በሆዷ ስትይዝ ነው እናም ይሄንን ባወቀች ጊዜ ስለ ሁኔታው ለማወቅ ድንጋጤ ስሜት ውስጥ ሆና በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ሄደች…. ሀኪሙ የተሰማትን ስሜት የሌላ ሳይሆን የእርግዝና ስሜት እንደህነ ገልፀላት ዶሎሬስ ይሄንን ስትሰማ ክፉኛ ደነገጠች እንባ እየተናነቃትም ይሄ ፍፅሞ ሊሆን የለበትም አለች

ከልጆች የተለየ ክፍል እንኳን በሌለው በአንድ ቤት ውስጥ የድህነት ህይወት እየገፋች አሁን ያሉትንም የቤተሰቦቿን አባላት መመገብ እስከሚያቅታቸው በድህነት ሕይወቷን እንደምትገፋ ገልፃለት ይሄንን ፅንስ ማስወረድ አለብኝ አለቺው… ሆኖም ሀኪሙ ፅንሱን ማስወረድ በህይወቷ ላይ ችግር ሊያስከትልባት ስለሚችል ይሄን ማድረግ እንዴሌለባት ገለፀላት

ሀኪሙ ይሄንን ይበል እንጂ የማሪያ ዶሎሬስ ፅንሱ መወለድ እንደሌለበት ወስና የሞቀ ቢራ ጠጥቶ መዝለል ፅንስ ያጨናግፋል ስባል ሰምታለችና ይሄንን ባልታሰበ ሰዓት የተከሰተባትን እርግዝና ለማቋረጥ የሞቀ ቢራ እየጠጣች መዝለል ጀመረች

ሆኖም ፅንስ ያጨናግፋል ሲባል የሰማቺው ባህላዊ አባባል እንዳሰበቺው ፅንሱን አልግዳውም እናም እርግዝናዋ ገፍቶ ልጁ ተወለደ

ባለቤቷ ጆሴ ዴኒስ አቨሮ በአንድ ወቅት የአሜሪካ ፕሬዝደንት የነበሩት ሮናልድ ድሬግን የህይወት ስኬት አድናቂ ነበሩና ለቤተሰቡ የመጨርሻ ልጅ ሆኖ የተወለደው ይሄን ህፃን ፕሬዝደንቱን ለማስታወስ ሮናልዶ ሲል ሰየመው

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ታላቅነት ጉዞ….

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ያለ አንዳች መሰልቸት ችሎታውን ለማጎልበት መስራቱን በመቀጠሉ የኳስ ችሎታው ከእለት ወደ እለት እያደገ ሄደ እናም በ 16 ዓመቱ የስፖርቲንግ ሊዝበን ዋና ቡድን ዓይን ውስጥ ገባ…. በክርስቲያኖ ሮናልዶ በግል ችሎታው የተደነቀው የስፖርቲንግ ሊዝበኑ አሰልጣኝ ወደ ክለቡ በማምጣት ለዋናው ቡድን እንዲጫወት መረጠው

August 2003 በዚች ቀን የሮናልዶ አዲስ ቡድን እና ማንችስተር ዩናይትድ የወዳጅነት ጨዋታ ያደረጉበት እለት ነው… እናም የሊዝበኑ አሰልጣኝ ወደ ቡድኑ የቀላቀለውን ሮናልዶ ለዚ ግጥሚያ አስፈረመው…

ከ ማንችስተር ዩናይትድ ጋር ባደረጉት በዚ ጨዋታም ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ብድኑ ማንችስተር ዩናይትድን 3ለ1 እንዲያሸንፍ የኳስ ጥበቡን በሚገባ ሲያሳይ ዋለ እናም በእለቱ ድንቅ ብቃት በማሳየት የጨዋታው ኮከብ መባል የቻለውን ይሄንን ተጫዋች ካዩ ቡሃላ የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቾች ፓትሪክ ኤቭራ እና ሪዮ ፈርድናንድ ይሄ ወጣት ወድ ብድናቸው እንዲቀላቀል አሰልጣኛቸውን ሴሪ አሌክ ፈጉሰንን አጥብቆ መወትወት ያዙ

ታላቁ አሰልጣኝ አሌክ ፈርጉሰንም በእለቱ ጨዋታ የሮናልዶ የግል ጨዋታና በተለይም ኳስ የማንጠባጠብ እና በሀይለኛ ምቶች ስለ ተደነቁ ለክለቡ ሀላፊዎች በማሳወቅ በወቅቱ በእንግሊዝ በወቅቱ በእንግሊዝ የተጫዋቾች ዝውውር ክፍያ ከፍተኛ የሆነውን 12.2 ሚሊዮን ፖውንድ ከፍሎ ሮናልዶን አስፈረሙት

በወቅቱ እጅግ ውድ በሆነ ዋጋ ወደ ዩናይትድ ያመራው ሮናልዶ በክለቡ የ 7 ቁጥር ማልያ ተሰጠው የ Cr7 የስኬት ጉዞ እጅግ በጣም ፈጣን በሆነ መልኩ መጉዋዙን ቀጠለ

ወደ ማንችስተር ዩናይትድ በተዘዋወረበት የውድድር አመት 20 ግቦችን በማስቆጠር ብድናቸው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ አነሳ

ሮናልዶ ለመጀመር ጊዜ ፕሮፈሽናል ኳስ ተጫዋች ሆኖ ከተቀላከለው ከማን ዩናይትድ ጋር በነበረው የጨዋታ ዘመን እጅግ ስኬታማ ከመሆኑ በላይ በግሉ የመጀመሪያ የሆነውን ባሎንዶር ሽልማት ጊዜ ሆኖ አልፏል

ከዚያም ከ 2009 የውድድር አመት በፊት ማንችስተር ዩናይትድን ለቆ በ 80 ሚሊዮን ፓውንድ እና 1 ቢሊዮን በሚደርስ የውል ማፍረሻ ክፍያ ቀጣይ ማረፊያውን ወደ ስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ አደረገ

ከአመታት በፊት በአንድ እለት በሮናልዶ ቤት የሚላስ የሚቀምስ አንዳች ነገር ጠፋ እናም አባቱ ኪት ማን ሆኖ ከሚሰራበት ስታድዮም አጠገብ ካለ የማክ ዶናልድ መሸጫ በመሄድ በሩ ላይ ቆሞ አንኳኩ….

የማክ ዶናልድ ቤቱ አስተናጋጅ ወጣና ምን እንደሚፈልጉ ጠየቃቸው የሚበሉትን አጥቶ እንደመጡና የሚበላ ካለ እንዲሰጣቸው ለመኑ የልጆቹ ሁኔታ ያሳዘነው አስተናጋጅ በረሃብ ለታጠፈው የልጅነት አንጀታቸው የሚሆን ጥቂት ምግብ ሰጣቸው

ሮናልዶ በታዋቂው የቲቪ host ፒርስ ሞርጋን ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ሲያደርግ ስለዚህ ጉዳይ ስያስታወስ እንባ እየተናነቀው ነው አሁን ይሄ ሁሉ አልፏል ስኬት የሱ እጣ ፈንታ ሆኖ ዝና ገንዘብ እድል የግሉ ሆኗል

ይሄን ችሎታውን ለማሳደግ በየ እለቱ የሚለፋው የልጅነት ዘመኑን በአስከፊ ድህነት ያሳለፈው አሁን ላይ በዓለም ካሉ 7 ዝነኛ እግር ኳስ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው

በዋሲሁን ተስፋዬ ተዘጋቶ በ 4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ የቀረበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *