ቪክቶር ዮኬሬሽ ሁለት ግብ ባስቆጠረበት ጨዋታ አርሰናል አትሌቲኮ ማድሪድን 4 ለ 0 አሸንፏል
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ 3ኛ ዙር ጨዋታ በሜዳው አትሌቲኮ ማድሪድን ያስተናገደው አርሰናል በሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።
በኢምሬትስ በተደረገው ጨዋታ ቪክቶር ዮኬሬስ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ጋብርኤል ማርቲኔሊ እና ጋብርኤል ማጋሌሽ ቀሪዎቹን ግቦች አስቆጥረዋል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ በዚህ ዓመት ያደረጋቸውን ሦስቱንም የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋተዎች ሲያሸንፍ አንድም ግብ አልተቆጠረበትም።
መድፈኞቹ በውድድር ዓመቱ ካደረጓቸው 12 ጨዋታዎች በዘጠኙ ግብ ሳይቆጠርባቸው ወጥተዋል።
ባርሴሎና ኦሎምፒያኮስን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል። በጨዋተው ፈርሚን ሎፔዝ ሦስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል። ማርከስ ራሽፎርድ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር፣ ላሚን ያማል ቀሪዋን ግብ በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠረ ተጫዋች ሆኗል። በ2ኛው ጨዋታ በፒኤስጂ የተሸነፈው ባርሴሎና ወደ አሸናፊነት የተመለሰበትን ውጤትም አስመዝግቧል።
ማንችስተር ሰቲ ቪያሪያልን በሃለንድ እና በርናርዶ ሲልቫ ግቦች 2 ለ 0 አሸንፏል።
የባለፈው ዓመት የሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ፒኤስጂ ባየር ሊቨርኩሰንን 7 ለ 2 በሆነ ሰፊ ውጤት ያሸነፈ አሸንፏል
ከሜዳው ውጭ ከፒኤስቪ የተጫወተው ናፖሊ 6 ለ 2 የሆነ አስደንጋጭ ሽንፈት ግጠሞታል።
በሌሎች ጨዋተዎች ኒውካስትል ዩናየትድ ቤኔፊካን 3 ለ 0 ሲያሸንፍ ኢንተር ሚላን ሴንት ጊሎስን 4 ለ 0 አሸንፏል። ቦሩሲያ ዶርትሙንድም ከሜዳው ውጭ ኮፐንሀገንን በገጠመበት ጨዋታ 4 ለ 2አሸንፎ ተመልሷል።
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የ3ኛ ዙር መርሀ ግብር ትላንት በተደረጉ ዘጠኝ ጨዋታዎች ብቻ 43 ግቦች የተቆጠሩበት ሆኗል።
ወደ አጫጭር የዝውውር መረጃዎች ስናመራ
ሊቨርፑሎች በጥር የዝውውር መስኮት የበርንማውዙን ጋናዊ አጥቂ አንቶኒ ሴሜንዮን ለማስፈረም እያሰቡ ነው ተብሏል።
የኖቲንግሃም ፎረስቱ አማካይ ኤሊዮ አንደርሰን የማንቸስተር ዩናይትድ የዝውውር ኢላማ ሆኖ ብቅ ብሏል ሲል ሚረር ዘግቧል።
ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ኤንድሪክ በጥር ወር ሪያል ማድሪድን ለመልቀቅ ፍቃደኛ ነው ፣የ19 አመቱ ወኪል ተጭዋቹ በውሰት ሪያል ማድሪድን በመልቀቅ ወደ ሌላ ክለብ ሊዘዋወር የሚችልበትን ሁኔታ እየሰራ ነው።
ቶተንሃሞች የአል አህሊውን አጥቂ ኢቫን ቶኒን ለማስፈረም ወደ 60 ሚሊየን ዩሮ ለማቅረብ ፍቃደኞች እንደሆኑ ተዘግቧል።
ባርሴሎና አሁንም 138 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ክፍያ እዳ አለበት ከዚም ውስጥ 36.5 ሚሊዮን ፓውንድ ሊድስ ዩናይትድ እና 25 ሚሊዮን ፓውንድ ማንቸስተር ሲቲ እዳ ያለበት ክለቦች ናቸው
የማንቸስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የባርሴሎናውን አጥቂ ሮበርት ሌዋንዶውስኪን በሚቀጥለው ክረምት የማስፈረም ፍላጎት አላቸው ሲል ስታር ዘግቧል።
ቪንሴንት ኮምፓኒ ከባየር ሙኒክ ጋር እስከ ሰኔ 2029 ድረስ የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ፈርሟል !
ሃሪ ማጉየር ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ያለውን ኮንትራት ለማራዘም በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ነው። ተጫዋቹ ያንን ለማሳካት የደመወዝ ቅነሳን ለመቀበል ፈቃደኛ ነው:
ዌስትሃም አዲስ አጥቂ ለማስፈረም እየፈለጉ ሲሆን ኔዘርላንዳዊዉ አጥቂ ጆሹዋ ዚርክዚን እንደ አማራጭ ይዘዉታል። መዶሻዎቹ ሮማን ጨምሮ ከበርካታ የጣሊያን ክለቦች ፉክክር ይገጥማቸዋል።