• Fri. Nov 20th, 2026

ጥቅምት 14 2018 አ/ም አርብ የወጡ አጫጭር ስፖርታዊ ዜናዎችን…..

ByAdmin

Oct 24, 2025

የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቷ ሩት ችፕንጌቲች የሶስት ዓመት እገዳ ተጣለባት

***

ኬንያዊቷ የማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቷ  አትሌት ሩት ችፕንጌቲች አበረታች ንጥረ ነገር ተጠቅማ መገኝቷ በመረጋገጡ  ለሦስት ዓመት እገደ እንደተጣለባት ይፋ ሆኗል።

ቀደም ብሎ ከጉዳዩ ጋር በተገናኘ በጊዜያዊነት ታግዳ የነበረችው የ31 ዓመቷ አትሌት የጸረ አበረታች ቅመሞችን ህግ ተላልፋ መገኘቷን የአትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ይፋ አድርጓል።

ኬንያዊቷ አትሌት የተገኝባት (ሀይድሮክሎሮቲያዛይድ) የተባለ የተከለከለ መድሀኒት መሆኑን ይፋ ያደረገው አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ አትሌቷ ቅጣቱን መቀበሏንም አሳውቋል።

አበረታች ቅመሞችን ተጠቅማ መገኘቷ የተረጋገጠው የሦስት ጊዜ የቺካጎ ማራቶን አሸናፊዋ ሩት ችፕንጌቲች ከመጋቢት 14 ቀን 2025 በፊት ያስመዘገበቻቸው ስኬቶቿ እንደማይሰረዙ አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ይፋ አድርጓል።

በመሆኑም ከኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትግስት አሰፋ እጅ የወሰደችው የዓለም የማራቶን ክብረ ወሰን በራሷ በችፕንጌቲች እጅ ተይዞ የሚቆይም ይሆናል።

አበረታች ቅመሞችን የሚጠቀሙ ኬንያውያን አትሌቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ ሲሆን ከ2017 በኋላ ሩት ችፕንጌቲች የተከለከለ ንጥረ ነገር ተጠቅማ የተገኘች 140ኛዋ የኬንያ አትሌትም ሆናለች። ይሄ አስደንጋጭ ቁጥር ምስራቅ አፍሪካዊቷን ሀገር አበረታች ቅመሞችን በመጠቀም ቀዳሚዋ ሀገርም አድርጓታል።

ማራቶንን ከ2 ስአት ከ10 በታች መግባት የቻለችው የመጀመርያዋ አትሌት ሩት ችፕንጌቲች  የቺካጎ ማራቶንን የገባችበት 2 ስአት ከ9 ደቂቃ 56 ሰከንድ የአለም ክብረ ወሰን ሆኖ መመዝገቡም ይታወሳል፡፡

ማንቸስተር ዩናይትድ በቀጣይ አመት ሁለት አዳዲስ የመሀል ሜዳ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ተዘጋጅቷል ተጫዋቾቹም የቼልሲው አንድሬይ ሳንቶስ እና የብራይተኑ ካርሎስ ባሌባ ይገኙበታል። (Talksport) 

የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ በባርሴሎና መቆየት እንደሚፈለግ ተናግሯል፣ 

የኒውካስትል ዩናይትድ የ23 አመቱ ጀርመናዊ አጥቂ ኒክ ዎልቴማዴ ለባየር ሙኒክ ወደፊት ለመጫወት ተስፋ ያደርጋል ሲል ቢልድ ጋዜጣ ዘግቧል። 

ኤቨርተን ብራዚላዊውን አጥቂ ሪቻርሊሰንን እንደገና ለማስፈረም ዝግጁ ናቸው፣ ቶተንሃም የ28 አመቱን ተጫዋች በጥር ዝወውር መስኮት ላይ ለመሸጥ እያሰበ ነው ሲል Team Talk ዘግቧል። 

ኤሲ ሚላን፣ አስቶን ቪላ እና ዌስትሃም የ31 ዓመቱን የማንቸስተር ሲቲ አማካይ ማቲዮ ኮቫቺችን ለማስፈረም የሚፈልጉ ክለቦች ናቸው። 

የጀርመኑ ግብ ጠባቂ ማርክ-አንድሬ ተር ስቴገን በጥር ወር ባርሴሎናን ሊለቅ ይችላል ለ33 ዓመቱ ተጫዋች የእናስፈርምህ ጥያቄዎች ቀርበውለታል ሲል ስካይ ጀረመን ዘግቧል። 

ቼልሲ አዲስ ግብ ጠባቂ ማስፈረም ይፈልጋል  የ30 ዓመቱ የኤሲ ሚላን ተጫዋች ማይክ ማግናንን በሚቀጥለው ክረምት በነፃ ዝውውር ለማስፈረም ከመሞከሩ በፊት ለቴር ስቴገንን ከ ባርሴሎና በውሰት ሊያስፈርም ይችላል።

📸 የአለም ሻምፒዮን የሆነዉ የሞሮኮ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ሀገሩ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ሊዮ ሜሲ በኢንተር ማያሚ ቤት ያለውን ውል ለተጨማሪ 3 ዓመታት አራዝሟል !

By Admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *