ማንቸስተር ዩናይትድ ጀርመናዊውን የባየርን ሙኒክ አማካይ አሌክሳንደር ፓቭሎቪችንም ለማስፈርም እየተከታተሉ ነው።
ሪያል ማድሪድ ቱርካዊውን አጥቂ ኬናን ዪልዲዝን ከጁቬንቱስ ለማስፈረም 100 ሚሊዮን ዩ ለመክፈል ፈቃደኛ ነው ተብሏል።
ማንቸስተር ሲቲ፣ ቼልሲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ የጀርመኑ ክለብ ኮለን ተጫዋች ሴይድ ኤል ማላን ለማስፈረም ፍላጎት ካላቸው ክለቦች መካከል ይገኙበታል።
የብራዚላዊው አጥቂ ገብርኤል ጄሱስ በአርሰናል ቤት ቢያንስ እስከ 2027 ድረስ ሚያቆየውን ኮንትራት መፈረም ይፈልጋል።
የቀድሞዉ የቫሌንሲያ ፣ ሊቨርፑል ፣ ኢንተር ሚላን ፣ ቼልሲ ፣ ሪያል ማድሪድ እና ናፖሊ አሰልጣኝ እንዲሁም ሌሎች ብዙ የአዉሮፓ እና የቻይና ክለቦችን የማሰልጠን ታሪክ ያላቸዉ አሰልጣኝ ራፋኤል ቤኒቴዝ የግሪኩን ክለብ ፓናቲናይኮስን በሁለት አመት ዉል ለማሰልጠን ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ቤኒቴዝ የግሪኩ ክለብ በአሰልጣኝነት ታሪካቸዉ 17ኛ ክለባቸዉ የሚሆን ሲሆን በአመት £3.47 ሚፓ ክፍያን በማግኘትም በግሪክ ክለቦች ታሪክ ዉዱ ተከፋይ አሰልጣኝ እንደሚሆኑ ተነግሯል።
የባርሴሎናዉ ታዳጊ ኮከብ ላሚን ያማል ከ ኤል ክላሲኮ ጨዋታ በፊት ባደረገው ቃለ ምልልስ በሪያል ማድሪድ ላይ ጠንከር ያሉ ቃላትን ሰንዝሯል።
“ሪያል ማድሪዶች ሌባ ናቸዉ፤ከዘረፉ በኋላ ደግሞ ቅሬታ ያቀርባሉ” ሲል ተናግሯል።
በተጨማሪም “ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ቤርናባዉ ስሄድ ጎል አስቆጥሬያለሁ 4 ለ 0 አሸንፈናቸዋል” ድጋሚ 4 ለ 0 ታሸንፋላችሁ? ተብሎ ለተጠየቀዉ ጥያቄ ተከታዩን ምላሽ ሰጥቷል።
“አይ እንደዛ ማለት አልችልም ግን ድጋሚ 4 ለ 0 ልናሸንፋቸዉ እንችላለን” ሲል ገልጿል።
ሼፊልድ ዌንስደይ የ12 ነጥቦች ቅጣት ተላለፈበት !!
የእንግሊዝ ሻምፒዮንሺፑ ክለብ ሼፊልድ ዌንስደይ ክለቡ በገባበት ከባድ የገንዘብ ኪሳራ እንዲሁም ከክለቡ ደጋፊዎች በተነሳበት ከፍተኛ ተቃዉሞ ምክንያት ተቋሙን ወደ ጊዜያዊ አስተዳደር ስርዓት ዉስጥ እንዲገባ ወስኗል።
ጊዜያዊ አስተዳደሩም ክለቡን በጊዜያዊነት የመቆጣጠር ፣ ዉሳኔዎችን የማሳለፍ ፣ ክለቡ ከእዳዉ ነፃ እንዲሆን ወይም እዳዉ እንዲቀንስ የማድረግ እንዲሁም ክለቡ በአዲስ ባለቤት ስር እንዲወድቅ የአዲስ ባለቤት ፍለጋ ሀላፊነት ይኖርበታል።
የኢኤፌል [EFL] ህግ በበኩሉ ክለቦች ወደዚህ ስርዓት ዉስጥ ለመግባት ከወሰኑ የ12 ነጥብ ቅነሳ እንዲጣልባቸዉ ይደነግጋል።
ስለዚህም በህጉ መሰረት ጉጉቶቹ የ12 ነጥብ ቅነሳ የተጣለባቸዉ ሲሆን በዚህም የስድስት ነጥቦች እዳን (-6) በመያዝ በሻምፒዮንሺፑ የደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል።
ዛሬ የሚደረጉ ጨዋታዎች
🏴በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ
11:00 | ቼልሲ ከ ሰንደርላንድ
11:00 | ኒውካስትል ከ ፉልሃም
01:30 | ማን ዩናይትድ ከ ብራይተን
04:00 | ብሬንትፎርድ ከ ሊቨርፑል
🇪🇸በስፔን ላሊጋ
09:00 | ጂሮና ከ ሪያል ኦቪዶ
12:15 | ኢስፓኞል ከ አልቼ
01:30 | አትሌቲክ ቢልባኦ ከ ጌታፌ
04:00 | ቫሌንሲያ ከ ቪያሪያል
🇮🇹 በጣልያን ሴሪ ኤ
07:30 | ዩድንዜ ከ ካግላሪ
10:00 | ቦሎኛ ከ ፒሳ
10:00 | ፊዮረንትና ከ ሮማ
12:00 | ናፖሊ ከ ጄኖአ
03:45 | ጁቬንቱስ ከ ኤሲ ሚላን
🇩🇪በጀርመን ቡንደስሊጋ
10:30 | ኦግስበርግ ከ RB ሌፕዝሽ
10:30 | ሞንቼግላድባህ ከ ባየር ሙኒክ
10:30 | አይንትራክ ፍራንክፈርት ከ ሴንት ፓውሊ
10:30 | ሀምበርገር ከ ሀይደናየም
10:30 | ሀምበርገር ከ ሜንዝ
01:30 | ዶርትሙንድ ከ ኮለን
🇫🇷በፈረንሳይ ሊግ 1
12:15 | ብረስት ከ ፒኤስጂ
02:00 | ሞናኮ ከ ቱልስ
03:45 | ሌንስ ከ ማርሴ
🇪🇹በሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ
09:00 | ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ መድን
10:00 | ሲዳማ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ