• Fri. Nov 20th, 2026

የጣልያን ሴሪ አ በፈረንጆቹ 90 ዎቹ እነዚህ ታላላቅ ተጫዋቾች ነበሩት። በወቅቱ ጁቬንትስ በ 96 ’97 እና 98 በሻምፒየንስ ሊጉ ለፍጻሜ ደርሶ ነበር።

Byadmin

Oct 31, 2024

በ96 የልዊ ቫንሀልን አያክስስ አምስተርዳም በመለያ ምት አራት ለሁለት ረቶ ዋንጫውን አንስቷል።በ97 በዶርትመንድ ሶስት ለአንድ በ98 ደግሞ በሪያል ማድሪድ አንድ ለዜሮ ተረቶ ዋንጫውን አጥቷል።ማድሪድ በፔድራግ ሚሀቶቪች ብቸኛ ጎል ከ32 አመታት በኋላ የመድረኩን ዋንጫ ማንሳቱ ይታወሳል ል።( እንዲህ እንደ አሁኑ እንደ ሊግ ዋንጫ ሻምፒየንስ ሊጉን በተደጋጋሚ ከማንሳቱ በፊት የግዙፉ የአውሮፓ ክለቦች መድረክ ዋንጫ ለማሪንጌዎች እንደ ሰማይ የራቀበት ጊዜ ነበር።)

በ1994 የፋቢዮ ካፔሎ ኤሲ ሚላን የሁዋን ክራይፍን ባርሴሎና ሳይጠበቅ አራት ለዜሮ በመርታት የመድረኩን ዋንጫ አንስቷል። በ95 ደግሞ በወጣት ቡድን በተገነባው አያክስ አምስተርዳም ተረቶ ዋንጫውን አጥቷል። ተቀይሮ የገባው በወቅቱ 19 አመት ላይ የነበረው ፓትሪክ ክላይቨርት 85 ኛው ደቂቃ ላይ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ጎል ከመረብ አገናኝቷል።

ላዚዮ ፣ ኢንተር ሚላን እና ፓርማ ማክሰኞ ቀን ይደረግ በነበረው እና በተለምዶ የማህበረሰብ ዋንጫ ብለን በምንጠራው( የስሙ ባለቤት ይፈለግልኝ) እና ሀሙስ ይደረግ በነበረው ካፕ ዊነርስ ካፕ ውድድር ላይ እስከ ፍጻሜ በተደጋጋሚ ከመድረሳቸው በተጨማሪ ዋንጫውን ማንሳትም ችለዋል።

ዘጠናዎቹ ያለ ምንም ጥርጥር የጣልያን እግር ኳስ ክለቦች ጊዜ ነበር።

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *