ህልም፣ትጋት፣ጽናት፣ውጣ ውረድ እና በስኬት የታጀበው የአሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የ25 አመት የአሰልጣኝነት እና አስደማሚ ግለ ታሪክን የሚተርክ ዘጋቢ ፊልም ዛሬ በኢትዮጵያ ሆቴል ተመርቋል።
በኮራ ወንዝ ዳርቻ ከእረኝነት የጀመረው የአሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የህይወት ውጣ ውረድ አሁን ወደ ታላቅነት ተሸጋግሯል።
ባለፉት አመታት በኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ውስጥ በወርቃማ ብዕር ስሙን የጻፈው አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሰራቸውን ገድሎች የተረከው ይህ ዘጋቢ ፊልም ዛሬ ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሆቴል አድናቂዎቹና ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት በይፋ ይመረቃል።
በ25 አመት የአሰልጣኝነት ህይወቱ ከተለያዩ ክለቦች ጋር 26 ዋንጫዎችን አሸንፏል።
በሕይወት ሁሉ ውስጥ ሊገጥሙ የሚችሉ ፈተናዎችን ፊት ለፊት የተጋፈጠው አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግም ሰባት ዋንጫዎችን በማንሳት ሪከርዴን ሰቅሎት አስቀምጦታል ። በሊጉም አራት ተከታታይ ዋንጫዎችን በማንሳት ብቸኛው አሰልጣኝ ነው