• Fri. Nov 20th, 2026

የሻምፒዮንስ ሊጉ ኮከብ ያጋጠመው የመኪና አደጋ

Byadmin

Oct 31, 2024

የሻምፒዮንስ ሊጉ እና የቡንደስሊጋው ኮከብ ቪክቶር በኒሬስ በጣም አስደንጋጭ የሆነ የመኪና አደጋ ካጋጠመው በኋላ ክስተቱን በማህበራዊ ሚዲያዎች በኩል አጋርቶ ነበር፤ በተጫዋቹ ላይ አስከፊው የመኪና አደጋ ያጋጠመው  ባለፈው ሣምንት ቅዳሜ ነበር፡፡

በ23 አመት እድሜው ላይ የሚገኘው በኒሬስ በእለቱ የእሱ ክለብ የሆነው ባየር ሌቨርኩሰን ኢንትራክት ፍራንክፈርትን ባሸነፈበት ጨወታ ላይ ከመሳተፉም በተጨማሪ የአሸናፊነቷን ግብ ያስቆጠረውም ይኸው ናይጄሪያዊ አጥቂ ነበር፡፡ ይህም ሆነ በዚህ ጨዋታ ያጋጠመው ፈንጠዝያ በምሽት ባጋጠመው አደጋ ሊደበዝዝ መቻሉ ነው የተነገረው፡፡

ከአደጋው በኋላ በማህበራዊ ሚዲያዎች በኩል የተለቀቁት ፎቶዎች አንድ ከፊት ለፊት በቀኝ በኩል ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባትን ጥቁር የቤት መኪና ምስል ይዘው ወጥተዋል፡፡ ቤኒፊስም በደም የተጨማለቁ እጆቹን የሚያሳየውንና በሆስፒታሉ አልጋ ላይ ተኝቶ የሚታየውን ምስሉን አጋርቷል፡፡ ይህም ሆኖ ተጨዋቹ የደረሰበት ጉዳት ለክፉ የሚሰጠው እንዳልሆነ በማህበራዊ ሚዲያዎች በኩል የገለፀው “God is the  greatest’’ (ፈጣሪ ከሁሉም የላቀ ታላቅ ነው) የሚል የፅሁፍ መልዕክቱን በማጋራት ነበር፡፡

ቢኒፊሲ ከዚህ አደጋ በፊት ያልተለመዱ ነገሮች ገጥመውት ነበር፤በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ያለ  ምግብ፣ውሃና ስልክ ለ18 ሰዓታት ያህል ከታገዱት የናይጄሪያ  ብ/ቡድን አባላት ውስጥ ይገኝበት ነበር፡፡  “ይህ ሁኔታ አስፈሪ ነው፣ እኛ ወደ ሀገራችን መመለስ እንፈልጋለን” የሚለውን መልዕክት ፅፎ ነበር፡፡

ይህ እገታ የተከሰተው የናይጄሪያ ቡድን ከሊቢያ አቻው ጋር ከመጫወቱ በፊት በትሪፖሊው አብራቅ አየር መንገድ ውስጥ ነበር፡፡ 

“የቻርተርድ አውሮፕላኗ የናይጄሪያ ተጨዋቾችን እንደያዘች ባልተለመደ እና በጣም አደገኛ በሆነ መንገድ አቅጣጫዋን ቀይራ ከቤንጋዚ በሚርቅ አንድ የአውሮፕላን  ማረፊያ ላይ እንድታርፍ ተደረገ፤ የአል ኢብራቅ አለም አቀፍ አየር መንገድ ለሀጂ ተጓዦች ብቻ የተፈቀደ መሆኑን የተረዳነው ቆይቶ ነው፡፡ ያሉት ክፉኛ ከተጉላሉት ተጨዋቾች መካከል አንደኛው ነበር፡፡

የሊቢያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የናይጄሪያን ተጨዋቾች ለመቀበል አልሞከረም፣ ተጨዋቾቹን ወደ ሆቴላቸው የሚያደርስ መኪናም አልተላከላቸውም፤ ተጨዋቾቹን ወደ ሆቴላቸው የላካቸው የናይጄሪያ እግር ክስ ፌዴሬሽን ዘግየት ብሎ ያዘጋጃው መኪናዎች እንደነበርም ተጠቁሟል፡፡  ከዚያ እንግልት በኋላ ሳምንቱ ለተጨዋቾቹ ጥሩ እንዳልነበር ይሣያል፡፡VIA BEST SPORT

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *