ፖርቱጋላዊው አሰልጣኝ በስተመጨረሻ የቀያይ ሰይጠናቱ ቀጣይ አለቃ መሆኑን ክለቡ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ላይ አስታውቋል።
የ39 አመቱ የወቅቱ የስፖርቲንግ ሊዝበን አሰልጣኝ የኦልድትራፎርዱን ክለብ ሀላፊነት የሚረከበው ግን ከሀገራት ጨዋታዎች መልስ የክለብ ውድድሮች ሲመለሱ እንደሆነ ግን ተገልጿል።
በጊዜያዊነት ዩናይትድን እየመራ የሚገኘው ኔዘርላንዳዊ የቀድሞ ኮከብ አጥቂ ሩድ ቫኒስተርሎይ እስከዚያ ድረስ በሀላፊነት እየመራ እንደሚቆይም ተገልጿል።