• Fri. Nov 20th, 2026

ኤዱ ጋስፐር ከአርሰናል የስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሀላፊነቱ ለቀቀ

Byadmin

Nov 4, 2024

ብራዚላዊው በ2019 ከእግር ኳስ ተጫዋችነት ዘመን ሀላፊነቱ በኋላ በቴክኒካል ዳይሬክተርነት ከተቀላቀለ በኋላ በታህሳስ ወር 2022 በክለቡ ታሪክ የመጀመሪያው የስፖርቲንግ ዳይሬክተር በመሆን መሾሙ ይታወሳል።

የ46 አመቱ ኤዱ በፈረንጆቹ ከ2001-2005 በተጫዋችነት መድፈኞቹን ማገልገል የቻለ ሲሆን በቆይታው ሁለት የሊግ ዋንጫዎችን ሲያሳካ በ20003-04 የ’Invincibles” ቡድን አካልም ነበር።

የቀድሞ አማካይ ስፔናዊውን አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ ወደ ሀላፊነት በማምጣት በኩል ትልቅ ሚና የነበረው ሲሆን አርቴታ በመጀመሪያው የውድድር ዘመን ቆይታው የኤፍኤካፑን ማሸነፍ ችሎ ነበር።

ከዚያ ጊዜ በኋላ ቡድኑ ዋንጫ ማሳካት ያልቻለ ሲሆን ኤዱ ቡድኑ ባለፉት ሶስት የውድድር ዘመናት ላሳየው አስደናቂ ለውጥ ግን ከአርቴታ ጋር በመሆን የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። አርሰናል ባለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት የፕሪምየር ሊጉ ዋንጫ ተፎካካሪ በመሆን ማንቺስተር ሲቲን በመከተል ማጠናቀቅ ችሏል።

አምበሉ ማርቲን ኦዲጋርድ ቤን ዋይት ጋብርኤል ጄሱስ እና ዴክላን ራይስን የመሳሰሉ ተጫዋቾች የመጡትም በእሱ የሀላፊነት ዘመን ነው። ባሳለፍነው ቅዳሜ በኒውካስትል ዩናይትድ ሽንፈት ባስተናገደው የአርቴታ ቡድን ስብስብ ውስጥም ከአካዳሚ ውጤቱ ቡካዮ ሳካ ውጭ የቀሩት በእሱ ምልመላ የመጡ ናቸው። 

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *