• Fri. Nov 20th, 2026

ከውድቀት እስከ ስኬት የሮሜሎ ሉካኩ የህይወት ታሪክ

ByAdmin

Sep 26, 2025

በአለም እግርኳስ ከታዩ ምርጥ አጥቂዎች አንዱ ነው። በኤቨርተን ፣ በቼልሲ ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ : በሮማ እና ኢንተርሚላን ተጫውቷል። አሁንም በጣልያኑ ክለብ ናፖሊ እየተጫወተ ይገኛል። ለክለቡ እና ለሀገሩ ብዙ ጎሎች አስቆጥሯል። ብዙ ውጣ ውረዶች አሳልፏል ፣ የእለት ምግብ እስከማጣት ደርሰዋል ፣ እናቱ ለዳቦ የሚሆን ሳንቲም ሳይቀር ለልጆችዋ ስትል ተበድራለች ፣ ወተትን በውሃ እየቀላቀለ በልቷል ቤልጄማዊው አጥቂ ሮሜሎ ሉካኩ። ምንም ያልነበረንን ጊዜ በትክክል አስታውሰዋለሁ። እናቴ ከፍሪጅ አጠገብ ቆማ ፊቷን ስትመለከት አሁንም ድረስ በአእምሮየ ይታየኛል። የ6 አመት ህፃን ነበርኩ። ከት/ቤት ወደቤት ምሳ ለመብላት እመጣ ነበር እናቴ ግን በእያንዳንዱ ቀን ሁሌ የምታቀርብልኝ ምሳ አንድ አይነት ነበር። ሁሌ ዳቦ እና ወተት ነበር። በርግጥ ህፃን ስለነበርኩ ምንም አይሰማኝም ነበር። እንደተቸገሩ ተረድቻለሁ። ከእለታት አንድ ቀን ከት/ቤት መጥቼ ወደ ኪችን ሄድኩ እናቴ ከፍሪጅ ወተት አውጥታ መስጠት የተለመደ ቢሆንም የዛን ቀን ግን አንድ ነገር ስትደባልቅ ነበር ያየሁት፡፡ ወዴት እየሄድን እንደሆነ አልገባኝም ሁሉ ነገር በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ እየሳቀች ለኔ ምሳዬን ሰጠችኝ እውነታው ግን ተቃራኒ ነው ስትደባልቅ የነበረው ውሃውን ከወተቱ ጋር ነበር። ለሳምንት የሚበቃ ወተት መግዛት እንኳን አልቻለችም ደሀ ብቻ አልነበርንም በጣም ደሀ እንጂ አባቴ እግርኳስ ተጨዋች ነው፡፡ ግን የእግርኳስ ዘመኑ እያበቃ ነበር እና ገንዘባቸው ሁሉ ጨርሰው ስለነበርም ወደዕቃ መሸጥ ነበር የተገባው : መጀመሪያ የተሸጠው ዕቃም ቲቪ ነበር እግርኳስ የለም፣ ማች ኦፍ ዘ ዴይ የለም፣ ሲግናል የለም ከዛም በኋላ መብራት ባለመክፈላችን ተቋረጠ፡፡ ለ ሁለት ሦስት ሳምንታት ምንም መብራት የለንም ነበር ገላዬንም በሙቅ ውሀ መታጠብ እፈልግ ነበር ግን ሙቅ ውሀ የለም እናቴ ስቶቭ ላይ በማንቆርቆሪያ ውሀ አፍልታልኝ በጆክ ጭንቅላቴ ላይ እያፈሰስኩ ነበር የምታጠበው እናቴ ዳቦ እንኳን መንገድ ዳር ካለ ዳቦ ቤት ትበደራለች ዳቦ ቤቶቹ እኔንና ታናሽ ወንድሜን ስለሚያውቁን ለሳምንት ብድር ይሰጧታል። 

የሳምንቱ መጨረሻ ላይ ትከፍላለች ግን አሁንም እናቴ ውሃውን ከወተቱ ጋር እያደባለቀች ነበር የምትሰጠኝ ይሄ እውነታው ነው የኛ ቤተሰብ ህይወት ነው ለሷ ምንም ቃል አልናገርም እንድትጨነቅም አልፈልግም ዝምብዬ ምሳዬን እበላ ነበር ብዙ ቀኖች ከት/ቤት ወደ ቤት ስመጣ እናቴን እያለቀሰች አገኘኋት። በመጨረሻም እንዲህ አልኳት “እናቴ ሁሉ ነገር ይቀየራል ታያለሽ እኔ ለአንደርሌክት እግር ኳስ እጫወታለሁ። የአንደርሌክት ተጨዋች እሆናለሁ፡፡ ሁሉም ጥሩ ይሆናል ምንም አትስጊ ስድስት ዓመቴ ነበር። አባቴን ፕሮፌሽናል እግርኳስ በስንት ዓመት ነው የሚጀመረው ብዬ ጠየኩት፡፡ አስራስድስት አለኝ እሽ አስራስድስት ብዬ ያን ለማሳካት ጉዞ ጀመርኩ እያንዳንዱን ጨዋታ እንደ ፍፃሜ ቆጥሬ ነው እጫወታለሁ። በኬጂ እንኳን እረፍት ሰዓት ላይ እንደ ፍፃሜ ነው የምጫወተው ቁመቴ እያደገ ሲመጣም አንዳንድ አስተማሪዎችና ወላጆች እኔን ጠበቅ አደረጉኝ። አንድ ቀን አንድ ተለቅ ያለ ሰው ወደ እኔ ቀረብ አለ እና “ስንት አመትክ ነው? መቼ ነው የተወለድከው” እያለ በጥያቄ አጣደፈኝ። በጊዜው 11 ዓመቴ ነበር። ለሌሪስ የወጣቶች ቡድን እጫወት ነበር።የኔ እድሜ ሲጠይቅ የነበረ ሰውም ሜዳ እንዳልገባ ሊያስቀረኝ ከጫፍ ደርሶ ነበር። እንደገና እዛ ለነበሩ ሰዎች “ስንት ዓመቱ ነው ይሄ ልጅ? የታለ መታወቂያው? ከየት ነው የመጣው?” ሲል በተደጋጋሚ ድምፁ ከፍ አድርጎ ሲጠይቅ አስታውሳለሁ። እኔም መለስኩ “የተወለድኩት አንትወርፕ ቤልጅየም ነው ቤልጄማዊ ነኝ” አልኩ። በርግጥ አባቴ በዚያ የጨዋታ ቀን አልነበረም ከሜዳ ውጭ የሆኑ ግጥሚያዎች ላይ መኪና ስለሌለው አይመጣም ነበር። ከሁሉም እኔን ብቻ ነው የጠየቁኝ፡፡ ከቦርሳዬ መታወቂያዬን አውጥቼ ለሁሉም ወላጆች አሳይቼ ገባው። ስገባም በውስጤ የታመቀ በቀል በሚመስል ሁኔታ “ቆይ ልጆቻችሁ እያለቀሱ ወደ ቤት ይመለሳሉ” እያልኩኝ በንዴት። በእግርኳስ የቤልጄም ኮኮብ ተጨዋች መሆን እፈልጋለሁ። ህልሜ የነበረው ጥሩ  ወይም የተሻለ ተጨዋች መሆን ሳይሆን የቤልጄም ምርጥ ተጨዋች መሆን ነበር። ህልሜ ትልቅ ስለነበረ ሁሌ ስጫወት እልህ እና ቁጭት በተሞላበት ነው። ሰዎች እኔ ላይ የነበራቸው አመለካከት ፣ ቤታችን ውስጥ በነበሩ አይጦች ምክንያት የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ እንኳን እንዳላይ በማድረጋቸው እና ቤታችን ውስጥ የነበረው እጅግ አስከፊ ድህነት እኔ በተሻለ መንገድ እንድጫወት አድርገውኛል። 12 አመት በነበርኩበት ጊዜ በ34 ጨዋታዎች 76 ጊዜ መረብ እና ኳስ ማገናኘት ቻልኩ። የሚገርመው እነዚህ 76 ጎሎች ያስቆጠርኳቸው በአባቴ ጫማ ነበር። አያቴ በእኔ ትልቅ ቦታ ያለው ሰው ነው። እናም 76 ጎሎች ካስቆጠርኩ በኋላ ለአያቴ ደወልኩለት።

ሞቅ ያለ ጨዋታ እየተጨዋወትን 76 ጎሎች እንዳስቆጠርኩ፣ ዋንጫ እንዳሸነፍን እና በታላላቅ ቡድኖች አይን ውስጥ እንደገቡ ነገርኩት። አያቴ ስለእኔ የእግርኳስ ሁኔታ ማወቅ ይፈልጋል። ስለእኔ እግርኳስ መስማት ያስደስተዋል። በዛን ቀን አያቴ ከወትሮ በተለየ ተቀየረብኝ። እንዲህም አለኝ። “ኦኦ ሮም ልጄ በጣም ደስ ይላል ፣ ነገር ግን አንድ ነገር ውለታ ልትውልልኝ ትችላለክ?” አለኝ። እኔም ” አዎ ምንድነው?” ብየ ጠየኩቴ።  አያቴም “ልጄን በደንብ ልትንከባከብልኝ ትችላለህ” ብሎ ሲጠይቀኝ በጣም ግራ ተጋብቼ እንደነበረ አስታውሳለሁ። “ከእናቴ ሰላም ነን ምንም አታስብ” አልኩት። “አይ ቃል ግባልኝ ፣ ቃል ልትገባልኝ ትችላለህ፣ ተንከባከባት አደራ ፣ ለእኔ ስትል መከታ ሁናት እሺ” እያለ ቃል አስገባኝ። “እሺ አያቴ አታስብ ቃል እገባልሀለው ” ብዬው ስልኩን ዘጋሁት ። ስልክ ባወራንበት በአምስተኛው ቀን አያቴ ከዚህ አለም በሞት ተለየ፣ ከዛም ምን ሊለኝ እንደፈለገ በደንብ ገባኝ ። በጣም ነበር ያስከፋኝ ምክንያቱም አራት አመታትን በህይወት ኖሮልኝ ቢሆን ኖሮ ለ አንደርሌክት ስጫወት ቢያየኝ ደስ ይለኝ ነበር ፣ ቃሌን እንዳከበርኩ ቢያይ እና ሁሉም ነገር ጥሩ እንደሆነ ቢያይ ኖሮ በጣም ደስ ይለኝ ነበር። ቃል የገባሁትን ለእናቴ በአስራ ስድስት አመቴ እንደማደርገው ነግሬያት ነበር። በርግጥ በአስራ አንድ ቀናቶች ብቻ ዘግይቻለው። ግንቦት 29/2009  የጥሎ ማለፍ የፍፃሜ ጨዋታ – አንደርሌክት ከ ስታንዳርድ ሌግ ነበር። ፍፁም የማልረሳው በህይወቴ ልዩ ቀን ነበር ፣ ነገር ግን ለትንሽ ደቂቃ ወደ ኋላ ልመልሳችሁ ፣ ምክንያቱም በውድድር ዓመቱ መጀመሪያ ላይ ለአንደርሌክት ከ 19 ዓመት በታች ቡድን ተጫውቻለሁ። አሰልጣኜ ተቀይሬ እንድገባ ነገረኝ ፣ በውስጤ ግን ይመላለስ የነበረው ተቀይሬ እየገባሁ የምጫወት ከሆነ መቼ ነው ለዋናው ቡድን የምጫወተው የሚለው ጥያቄ ነበር ።  ስለዚህ ከ አሰልጣኙ ጋር ተወራረድኩ። እንዲህ አልኩት “አንድ ማረጋገጫ ልስጥክ ፣ የምታሰልፈኝ ከሆነ እስከ ታህሳስ ድረስ ሀያ አምስት ጎሎችን አስቆጥራለው” ስለው የእውነት ሳቀብኝ። እኔም “እንወራረድ” አልኩት። “እሺ ነገር ግን በአንድ መስፈርት በመስከረም ወር ሀያ አምስት ጎሎችን ካላስቆጠርክ ተጠባባቂ ወንበር ላይ ትቀመጣለክ” አለኝ ። “ጥሩ ፣ነገር ግን የማሸንፍ ከሆነ ከልምምድ ቦታ ወደ ቤታችን የሚያመላልሱን ሚኒቫንስ መኪኖችም ጭምር ታፀዳለህ“ አልኩት። አሰልጣኙም “ተስማምተናል” አለኝ። የመጨረሻ አንድ  ነገር ልጨምርልክ “ፓን ኬክ በየቀኑም ትሰራልናለክ” አሁንም እሺ ችግር የለውም በማለት በውርርዳችን ተስማማ ። ይህ በህይወት ዘመኔ ያደረኩት በጣም ጅል የሆነ ውርርድ ነው። ይሁንና ቃሌን ፈፀምኩ። በህዳር ወር እኔ ሀያ አምስት ጎሎችን አስቆጠርኩኝ ፣ ከገና በዓል በፊት በየቀኑ የፓን ኬክ እየበላን ነበር። ይህም እንደ ትምህርት ሆኖ አለፈ  ፣ ከተራበ ሰው ጋር ምንም አይነት ነገር አትጫወትም።

የመጀመሪያ ኮንትራቴን ከ አንደርሌክት ጋር የተፈራረምኩት በልደት ቀኔ ግንቦት 5 ነበር ፣ ከተፈራረምኩኝ በኋላ ቀጥታ ወደ ሱቅ በመሄድ የፊፋ ቪድዮ መጫወቻ ገዛሁ….። በዋናው የአንደርሌክት ቡድንም አስገራሚ ብቃትን በማሳየት በ76 ጨዋታዎች 33 ግቦችን አስቆጥሮ የመላው አውሮፓን ትላልቅ ቡድኖችን ትኩረት መሳብ ቻለ ። በመጨረሻም እ.አ.አ ኦገስት 2011 ላይ የእንግሊዙን ታላቅ ክለብ ቼልሲን በ20 ሚሊዮን ዩሮ እና በ5 ዓመት ኮንትራት መቀላቀል ቻለ በመቀጠልም በኤቨርተን እና በማንችስተር ዩናይትድ ቤቶች ከባድ በሆነው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በድምሩ በ278 ጨዋታዎች 128 ግቦችን በማስቆጠር በሊጉ ከታዩ ምርጥ አጥቂዎች መካከል አንዱ በመሆን ስሙን ማፃፍ ችሏል ። በዚህ ብቻ ያላበቃው ሉካኩ ወደ ሴሪአው በማቅናትም በኢንተር እና ሮማ መለያ መጫወት የቻለ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በሻምፒዮኖቹ ናፖሊ ቤት በመጫወት ላይ ይገኛል ። እኛም ከከፍተኛ ድህነት ተነስቶ ዛሬ ላይ በዓለም ከሚገኙ ምርጥ አጥቂዎች መካከል አንዱ መሆን የቻለውን የሮሜሎ ሉካኩን የህይወት ታሪክ የዳሰስንበት ፕሮግራማችን ይህን ይመስል ነበር !

By Admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *