• Fri. Nov 20th, 2026

ሐሙስ የወጡ አጫጭር ስፖርታዊ ዜናዎች

ByAdmin

Oct 16, 2025

ቪኒ ጎረቤት በመረበሽ ተከሰሰ..ፍራንኪ ዲ ዮንግ ውሉን በባርሴሎና ቤት አድሷል…ቶተንሀም ሀሪ ኬንን የግሉ ለማድርግ ቆርጦ ተንስቷል! ጥቅምት 6/2018 ዓ ም ሐሙስ የወጡ አጫጭር ስፖርታዊ ዜናዎች

ኒዘርላንዳዊው አማካይ ፍራንኪ ዲ ዮንግ ከካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ጋር እስከ 2029 ለመቆየት ነው ውሉን ያራዘመው።

በ2019 ከአያክስ አምስተርዳም ባርሴሎናን የተቀላቀለው አማካዩ በስድስት ዓመት ቆይታው 183 ጨዋተዎችን አድርጎ 14 ግቦችን አስቆጥሯል።

ማንቸስተር ሲቲ በሚቀጥለው ክረምት የኖቲንግሃም ፎረስት አማካኝ ኤሊዮ አንደርሰንን ለማስፈረም 75 ሚሊዮን ፓውንድ ለማውጣት አቅደዋል ነገርግን ሲቲዎቹ እንግሊዛዊውን ተጫዋች የግሉ ለማድረግ ከቼልሲ ጠንካራ ፉክክር ሊገጥመው ይችላል ሲል ኤክስፕረስ ዘግቧል።

ቶተንሀም በሚቀጥለው ክረምት ሃሪ ኬንን ከባየር ሙኒክ ለማስፈረም እየተዘጋጁ ነው የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም የቅድሞ ተጫዋቹን የግሉ ለማድረግ የውል ማፍረሻ እና የደመወዝ ጥያቄን ለማሟላት ተዘጋጅተዋል።

ማንቸስተር ዩናይትዶች በክረምት የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት አጥቂ የማስፈረም ፍላጎት አላቸው ኢላማ ያደረጉትም ጣሊያናዊ የፊት መስመር ተጫዋች ማቲዎ ሬቴጊን ሲሆን ሩበን አሞሪም ከሳውዲ ፕሮ ሊግ ክለብ አል ቃድሲያ ለማስፈረም እስከ 52 ሚሊዮን ዩሮ ለማውጣት ተዘጋጅተዋል።

ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ የ26 አመቱን የባየር ሙኒክ ተከላካይ ዳዮት ኡፓሜካኖን በነፃ ዝውውር በሚቀጥለው ክረምት ለማስፈረም እንቅስቃሴ ያደርጋሉ ነገርግን ማንቸስተር ዩናይትድም የተጫዋቹ ፈላጊ ነው ሲል ፉት መርካቶ ዘግቧል ።

ሮማ የማንቸስተር ዩናይትዱን አጥቂ ጆሹዋ ዚርክዜን የግሉ ማድረግ ይፈልጋል።

ጁቬንቱስ ላለፉት 6 ወራት የተከላካዮቻቸውን አማካኝቱራምንን ለማስፈረም ከፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አርሰናል ፣ ቼልሲ እና ሊቨርፑል የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

ስዊዲን አሰልጣኝ ጆን ዳህል ቶማሰንን ካሰናበተች በኋላ አሰልጣኝ በማፈላለግ ላይ ትገኛለች።

በዓለም ዋንጫ ማጣሪያው ምድብ ሁለት ላይ የምትገኝው ስዊድን በአንድ ነጥብ የምድቡ ግርጌ ላይ ተቀምጣለች።

የቀድሞው የቼልሲ እና የብራይተን አሰልጣኝ ግርሀም ፖተር የስዊድን ብሔራዊን ለማሰልጠን ፍላጎት ማሳየታቸውን ስካይ ስፖርት ዘግቧል።

የ2025 የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ዕጩዎች ይፋ ሆኑ


በአንድ የውድድር ዓመት ስኬታማ የሆኑ ወጣቶች እውቅና በሚያገኙበት ሽልማት  25 ወጣቶች በዕጩነት ቀርበዋል፡፡

ቱቶስፖርት በሚያዘጋጀው የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች (golden boy) ሽልማት የፒኤስጂውን ዲዘር ዱዌ እና የማንችስተር ዩናይትዱን ሌኒ ዩሮ ጨምሮ ፈረንሳይ ስድስት ተጫዋቾችን በዕጩነት አስመርጣለች፡፡

ዕድሜያቸው ከ21 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች እውቅና በሚያገኙበት የአርሰናሉ ኢታን ንዋኔሪ፣ የዶርትሙንዱ ጆብ ቢሊንግሀም፣ የባሴሎናው ፓው ኩባርሲ፣ እና የጁቬንቱስ ኬናን ይልዲዝ በዕጩነት ከቀረቡት መካከል ናቸው፡፡

ሽልማቱ በዚህ ዓመት ለ23ኛ ጊዜ የሚደረግ ሲሆን የባርሴሎናው ላሚን ያማል የባለፈው ዓመት አሸናፊ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ቪኒሺየስ ጁኒየር ከጎረቤቶች በተነሳ ቅሬታ ምክንያት በብራዚል ፖሊስ ተከሷል።

ቪኒ በሀገሩ ምደር ላይ እኔ ነኝ ያለ ትልቅ ፓርቲ በቤቱ አዘጋጅቶ ነበር ታዲያ በፓርቲው ፕርግራም ላይ ብዙ  ጫጫታዎችን በማሰማቱ ጎረቤቶች ቅሬታ እንዲያሰሙ አድርጓል።

ፖሊስም ተጠርቶ ቪኒሲየስ ሙዚቃውን እንዲቀንስ አስገደደው እሱ ግን የለም እንደዛ አላደርግም አለ ከጥቂት መከራከሮች ቡሃላ እሺ ብሎ ፖሊሶች ወደ ጣቢያቸው ድምፅ አስቀንሰውት ሄዱ

እሺ ብሎ የነበረው ቪኒ ታዲያ ግን በድጋሚ ፖሊሶቹ ከሄዱ በኋላ እንደገና ሙዚቃውን ከፍ አርጎ መቀወጡን ቀጠለው ፖሊሶቹም ከደቂቃዎች ቡሃላ በድጋሚ ተመልሰው መጥተው  “ሙዚቃውን አታስጭው  አላልንህም ታዲያ ለምን ጎረቤቶች ትረብሻለው እነሱ ናቸው ተረበሽን ብለው የደወሉት ሰለዚህ ዕረፍ ብለውት አስጠንቅቀውት በድጋሚ ይመለሳሉ

ቪኒሲየስ እንደገና እነሱ ከመሄዳቸው ሀትሪክ ሰራ ድምፁን በሙዚቃ ከማስጮህ አልፎ ጭራሽ ርችትም መተኮስ ጀመረ ፖሊሶችም በድጋሚ መጡ  ይህንን ተከትሎ ፖሊሶች አሁን ላይ ቪኒ ላይ ክስ መመሰረታቸው ተገልጿል።

By Admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *