• Fri. Nov 20th, 2026

ጥቅምት 7 ስፖርታዊ ዜናዎች | ብሩኖ ወደ ሙኒክ  | ኒኮ ዊሊያምስ ወደ ሊቬ | ራሽፎርድ ስለ ማንቼ ችግር ተናግሯል | ዴምቤሌ ተጨማሪ የደሞዝ ጥያቄ…

ByAdmin

Oct 17, 2025

ማንቸስተር ዩናይትዶች ብሩኖ ፈርናንዴዝን ወደ አውሮፓ ክለቦች ለመሸጥ £40 ሚሊዮን ዩሮ ይፈልጋሉ። የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ፖርቹጋላዊውን አማካኝ ማስፈረም ይፈልጋል ሲል Team talk አስነብቧል።

ሊቨርፑሎች የ23 አመቱን ስፔናዊ የአትሌቲክ ክለብ አጥቂ ኒኮ ዊሊያምስን በ 90 ሚሊዮን ዩሮ ለማስፈረም ተጫዋቹ ላይ አይናቸውን ጥሏል!

በተያያዘ ዜና ሊቨርፑል የቦሩሲያ ዶርትሙንዱን ተከላካይ ኒኮ ሽሎተርቤክን በክረምት የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት የጀርመኑ ክለብ የዝውውር ጥያቄ  እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል ተብሏል። 

የስፔኑ ክለብ ባርሴሎና የ 25 አመቱን ሰርቢያዊ የጁቬንቱስ አጥቂ ዱሳን ቭላሆቪች ለማዘዋወር እያጤነ ሲሆን ተጫዋቹ በሚቀጥለው ክረምት ከወኪል ነፃ  ይሆናል። 

ሪያል ማድሪድ የ26 አመቱን የባየር ሙኒክ ተከላካይ ዳዮት ኡፓሜካኖን በቅርበት እየተከታተሉት ሲሆን የፈረንሳዊው ኢንተርናሽናል ተጫዋች በሚቀጥለው ክረምት ኮንትራቱ ሲጠናቀቅ የዝውውር ጥያቄዎችን ለማዳመጥ ተዘጋጅተዋል።

ባርሴሎና የ 23 አመቱ የሆፈንሃይምን እና የኮሶቮ አጥቂ ፊስኒክ አስላኒን ለማስፈረም እየተመለከቱ ሲሆን ተጫዋቹ በሚቀጥለው ክረምት የጀርመኑን ክለብ ሊለቅ ይችላል።

በአዲስ ኮንትራት ዙሪያ ከፔዤ ጋር ድርድር ላይ የሚገኘው ኦስማን ዴንቤሌ የደሞዝ ጭማሪ ክለቡን ጠይቋል !

አሁን ላይ 18 ሚሊዮን ዮሮ በዓመት የሚያገኘው ኦስማን በተወሰነ ፐርሰንተ ደሞዙ ከፍ እንዲልለት ክለቡን ጠይቋል ሲል ሌኪፕ አስነብቧል።

ኦሊምፒክ ማርሴ አንድሪክን ለማስፈረም ፍላጎት ያሳዩ ሲሆን በቅርቡ ድርድር ለመጀመር እንቅስቃሴ ጀምረዋል

በአንድ አመት ውሰት ውል ወደ ባርሴሎና በማምራት እየተጫወተ የሚገኘው እንግሊዛዊ ኢንተርናሽናል አጥቂ በኦልድትራፎርዱ ክለብ ለነበረው አስቸጋሪ ቆይታ መጥፎ ከባቢ መኖሩን ምክንያት አድርጓል።  ራሽፎርድ የካታሎኑን ክለብ ከተቀላቀለ በኋላ ሳቢ የሚባል እንቅስቃሴን በማድረግ ላይ ይገኛል። 

በአሰልጣኝ ሀንስ ፍሊክ ስር በ10 ጨዋታዎች ሶስት ጎሎችን ሲያስቆጥር አምስት የጎል ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። በእግር ኳስ ወጥነት ወሳኝ መሆኑን ራሽፎርድ ገልጾ በዩናይትድ ቤት ይህ አለመኖሩ ትልቅ ችግር መሆኑን ገልጿል።

ሳውዲ አረቢያ ለአለም ዋንጫ በማለፏ እያንዳንዱ የሳውዲ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች የ1 ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ አግኝተዋል

ብራዚል እና ሴኔጋል በሚቀጥለው ወር በኢምሬትስ ስታዲየም የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርጉ ይፋ ሁኗል 

ፊፋ ለ2026 የአለም ዋንጫ ከቅድመ ትኬት ሽያጭ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ትኬቶችን መሸጡን አስታውቋል።

በ2025 ከፍተኛ 10 ውድ ተከፋይ እግር ኳስ ተጫዋቾ ታዋቂው ፎርብስ ጋዜጣ ይፋ አድርጓል። 

1️⃣ 🇵🇹 ክርስቲያኖ ሮናልዶ – 239 ሚሊየን ዩሮ

2️⃣ 🇦🇷 ሊዮኔል ሜሲ -111 ሚሊየን ዩሮ

3️⃣ 🇫🇷 ካሪም ቤንዜማ – 89 ሚሊየን ዩሮ

4️⃣ 🇫🇷 ኪሊያን ምባፔ – 81 ሚሊየን ዩሮ

5️⃣ 🇳🇴 ኤርሊንግ ሀላንድ -68 ሚሊየን ዩሮ

6️⃣ 🇧🇷 ቪኒሺየስ ጁኒየር – 51 ሚሊየን ዩሮ

7️⃣ 🇪🇬 መሀመድ ሳላህ – 47 ሚሊየን ዩሮ

8️⃣ 🇸🇳 ሳዲዮ ማኔ – 46 ሚሊየን ዩሮ

9️⃣ 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿ጁድ ቤሊንግሃም – 38 ሚሊየን ዩሮ

🔟 🇪🇸 ላሚን ያማል – 37 ሚሊዮን ዩሮ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉ በዚህ ሳምንት ይመለሳል!

➜ የሊጉ መሪ አርሰናል በለንደን ደርቢ ወደ ክራቨን ኮቴጅ አምርቶ ፉልሃምን የሚገጥም ሲሆን 

➜ ሊቨርፑል የምንግዜም ተቀናቃኙን ማን,ዩናይትድን በአንፊልድ የሚያስተናግድ ይሆናል 

➜ ቼልሲ የውጥቴ ቀውስ ውስጥ ያለውን ኖቲንገሃም ወደ ከሜዳው ውጪ የሚያስተናግድ ይሆናል

➜ቶተንሃም በተከታታይ ሳምንት ወደ አሸናፊነት የተመለሰው አስቶንቪላ በሜዳው የሚያስተናግድ ይሆናል 

➜ማን,ሲቲ ዘንድሮ በዴቪድ ሞይስ ስር ጠንካራ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘውን ኤቨርተን የሚያስተናግድ ይሆናል በሜዳው

By Admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *