የሚካኤል አርቴታ ቡድን ባለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት በፕሪሚየር ሊጉ የፔፕ ጋርዲዮላው ማንቺስተር ሲቲ አይነተኛ የሊግ ዋንጫ ተፎካካሪ ቡድን ሆኖ መታየት ችሏል።
በያዝነው የውድድር ዘመን ግን ከአስር የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ መርሀ ግብሮች በኋላ ከመሪው ሊቨርፑል በሰባት ነጥቦች አንሶ አምስተኛ ስፍራ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል።
ብላክብርን ሮቨርስ በ1994 ከአስር ጨዋታዎች በኋላ በወቅቱ መሪ ከነበረው ኒውካስትል ዩናይትድ በስምንት ነጥቦች አንሶ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ሻምፒዮን መሆን የቻለው ክለብ ነበር።
በወቅቱ ግን የኬኒ ዳግሊሽ ስብስብ ከመሪዎቹ ያነሰ የጨዋታ ቁጥር አድርጎ ነበር።
በተመሳሳይ በ2002-23 ማንቺስተር ዩናይትድ በ2013-14 እና 2020-21 ማንቺስተር ሲቲ ከመሪው ክለብ በስድስት ነጥብ ከአስር የጨዋታ መርሀ ግብር በኋላ አንሰው ተቀምጠው በስተመጨረሻ ሻምፒዮን መሆን የቻሉ ክለቦች ናቸው።
አርሰናል በተከታታይ ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ድል ማድረግ አልቻለም። አምና በሙሉ የውድድር ዘመኑ ከጣላቸው ነጥቦች ዘንድሮ ከወዲሁ ግማሹን ጥሏል።
የአርሰናል ደካማ ጉዞ በቁጥሮች
አርሰናል ከመጨረሻ ስድስት የሊግ ጨዋታዎቹ በአራቱ አንድ ለዜሮ ተመርቷል። ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ቁጥርን ያስመዘገበው በሰላሳ አንድ ጨዋታዎች ነው።
መድፈኞቹ በተከታታይ ሶስት የሜዳው ውጭ ጨዋታዎች ጎሎችን አስተናግደዋል።በታህሳስ ወር ሚኬል አርቴታ ሀላፊነቱን ከተረከበ በኋላም እንዲህ አይነት መጥፎ ሪከርድ ሲያስመዘግቡ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
በ2024 በ25 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግደው የነበሩት በአንዱ ብቻ የነበረ ሲሆን በሀያ አንዱ ድል ሲቀናቸው በሶስቱ አቻ ተለያይተው ነበር። ከመጨረሻ ሶስት የሜዳ ውጭ ጨዋታቸው ውስጥ ግን በሁለቱ ተረታው በአንዱ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
አርሰናል ከ2022 ግንቦት ወር በኋላም ለመጀመሪያ ጊዜ በተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሽንፈት አስተናግዷል።
በፕሪሚየር ሊጉ በያዝነው የውድድር ዘመን ከሜዳው ውጭ ጥቂት ሹቶችን 37 በማድረግ (7.4 በአማካይ በጨዋታ) ከብሬንትፎርድ 30 ( 7.5 በጨዋታ) ቀጥለው ተቀምጠዋል።