• Fri. Nov 20th, 2026

“ምራቄን የተፋሁት በማጨሳቸው ሁለት ወይም ሶስት ሲጋራዎች ምክንያት ነው” ኢቫንጄሎስ ማሪናኪስ

Byadmin

Nov 5, 2024

የኖቲንግሀም ፎረስቱ ባለቤት ኢቫንጄሎስ ማሪናኪስ ቡድናቸው በፉልሀም በተሸነፈበት ጨዋታ ላይ ዳኞቹ ላይ ምራቃቸውን ተፍተዋል በሚል ክስ የአምስት ጨዋታ እግድ ተቀባይነት እንዳገኘ ታውቋል፡፡

የ57 አመቱ ግሪካዊው ባለሀብት ማሪናኪስ በ6ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሲቲ ግራውንድ ኖቲንግሀም በፉልሃም 1-0 በተሸነፈበት ጨዋታ በዳኞች ላይ ምራቅ በመትፋት ያልተገባ ተግባር ፈጽመዋል በሚል ክስ እንደቀረበባቸው እና አምስት ጨዋታዎች ወደ ስታዲየም እንዳይገቡ መታገዳቸው ይታወሳል፡፡

ክስተቱ የተከሰተው በፕሪምየር ሊጉ 3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ኖቲንግሀም ፎረስት በፉልሃም በ VAR የፍፁም ቅጣት ምት ከተሸነፈ በኋላ የመሀል ዳኛው ጆሽ ስሚዝ፣ ረዳት ዳኛው ጀምስ ማይዋሪንግ እና አራተኛው ዳኛ ቲም ሮቢንሰን ወደ መልበሻ ክፍል ሲያመሩ ማሪናኪስ ምራቃቸውን ሲተፉ በመታየታቸው ነው ተብሏል፡፡

ባለሀብቱ ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸውም የአምስት ጨዋታ የስታዲየም እግድ የተጣለባቸው ሲሆን የጠየቁት ይግባኝም ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።

ባለሀብቱ ባቀረቡት ማስተባበያም የሳል ህመም ይዞኝ ነው እንጂ በዳኛው ላይ አስቤ አላደረግኩም በማለት ተናግረዋል።

አክለውም ሳሉ እና መትፋቱ በየቀኑ በማጨሳቸው ሁለት ወይም ሶስት ሲጋራዎች ምክንያት የመጣ ነው አስቤበት አይደለም ሲሉ ማስተባበያ ማቅረባቸው ተገልጿል።

ባለሀብቱ የሶስቱን ጨዋታዎች ቅጣት የጨረሱ ሲሆን በቀጣይ የኒውካስል እና አርሰናል ጨዋታዎች የሚያመልጧቸው ይሆናል።

✍️ይገደብ አባይ

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *