• Fri. Nov 20th, 2026

“ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች አዲስ ፈርጉሰን እንደመጣ ያስባሉ “ሩበን አሞሪም

Byadmin

Nov 5, 2024

የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ዛሬ ምሽት ስፖርቲንግ ከሲቲ የሚያደጉት ጨዋታ ይመለከቱታል ብየ አስባለሁ🤗

በቅርቡ ማንችስችተር ዩናይትድን በዋና ሀላፊነት የተቀጠሩት ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ዛሬ በሻምፒዮንስ ሊጉ ስፖርቲንግ ልዝበንን ይዘው ማንችስተር ሲቲን የሚያሸንፉ ከሆነ የዩናይትድ ደጋፊዎች አዲስ ፈርጉሰን እንደመጣ ያስባሉ ብለዋል፡፡

ከቀናት በፊት ማንችስተር ዩናይትድን በአሰልጣኝነት የተረከቡት ወጣቱ ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ከዛሬ ምሽቱ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ በፊት ለሚዲያ አካላት ሀሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

አሰልጣኙ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል ስለ ተጋጣሚያቸው ማንችስተር ሲቲ እንዲሁም በቅርቡ ስለሚረከቡት አዲሱ ክለባቸው ማንችስተር ዩናይትድ አንስተዋል፡፡

አሁን ላይ ስፖርቲንግ ሊዝበንን እያሰለጠኑ ያሉት አሞሪም ስለ ዛሬው ተጋጣሚያቸው ማንችስተር ሲቲ እንዳሉት፤ዛሬ የምንጫወተው ከምርጥ ቡድን ጋር ነው፤በእርግጠኝነት ከባድ ጨዋታ ይሆናል፤ማንችስተር ሲቲ ውስጥ ስለ ጉዳት ብዙ ይወራል ግን አብዛኞቹን ተጨዋቾች በመጨረሻው ጨዋታ እያየናቸው ነው ብለዋል፡፡

የዛሬውን ጨዋታ ከተሸነፍን ከእኔ የሚጠበቀው ነገር ይቀንሳል፤የምናሸንፍ ከሆነ ግን የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች አዲሱ ፈርጉሰን እንደመጣ ያስባሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም አሰልጣኙ ይህንን ብለዋል አሁን ላይ የእንግሊዙ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ ውስጥ ነገሮች ውስብስብ እና አስቸጋሪ ናቸው፤የምሄደው ውስብስብ ወደሆነ አለም ነው፤ነገርግን ነገሮችን ወደፊት ማራመድ አለብን በማለት ተናግረዋል።

በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የሚመራው ስፖርቲንግ ሊዝበን ዛሬ ምሽት 5 ሰአት ላይ ማንችስተር ሲቲን በሜዳው ይገጥማል፡፡

✍️ይገደብ አባይ

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *