ጋናዊው የዌስትሀም ዩናይትድ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ከቶተንሀም ሆትስፐር ጋር በነበረ የፕሪሚየር ሊጉ የለንደን ደርቢም መርሀ ግብር የቀይ ካርድ መመልከቱ የሚታወስ ነው።
ተጨዋቹ በወቅቱ በሰራው ጥፋት ምክንያት ከቀይ ካርድ በተጨማሪ የሁለት ጨዋታዎች ቅጣት እንደተጣለበት ይፋ ሆኗል።
በተጨማሪም ኩዱስ የ60ሺ ፓውንድ የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለበት ተነግሯል።
በዚህም መሰረት ጋናዊ ኢንተርናሽናል መዶሻዎቹ በቀጣይ ከኤቨርተን ኒውካስል ዩናይትድ እና አርሰናል ጋር የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች የሚያመልጡት ይሆናል ተብሏል ።