የማንቺስተር ዩናይትዱ ካሜሮናዊ ግብ ጠባቂ በአዲስ መጪው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ስር የማንቺስተር ዩናይትድ ተጫዋቾች ወደ ላይ ከፍ ማለት እንደሚችሉ ተናግሯል።
ዩናይትድ የስፖርቲንግ ሊዝበኑን አለቃ አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ በማድረግ መሾሙን ባሳለፍነው ሳምንት ማሳወቁ ይታወሳል።
ፖርቱጋላዊው ስራውን ከፈረንጆቹ ህዳር 11 አንስቶ በይፋ የሚጀምርም ይሆናል።
ጊዜያዊ አሰልጣኙ እና የቀድሞ የቡድኑ አጥቂ ሩድ ቫኒስተርሎይ በዚህ ሳምንት በዩሮፓ ሊግ እና በፕሪምየር ሊጉ ከፓኦክ እና ሌይስተር ሲቲ የሚደረጉ ጨዋታዎችን እየመራ የሚቆይም ይሆናል።