• Fri. Nov 20th, 2026

“አርሰናል አሁን ላይ የዋንጫ ተፎካካሪ አይደለም “ ቴሪ ኦንሪ

Byadmin

Nov 7, 2024

ፈረንሳዊው የቀድሞ የአርሰናል ታሪካዊ ተጨዋች ቴሪ ኦነሪ ትናንት ምሽት አርሰናል በኢንተር ሚላን ከተሸነፈ በኋላ በሰጠው አስተያየት ቡድኑ አሁን ላይ እያሳ ከሚገኘው ብቃት አንፃር ዘንድሮ ለፕርሚየር ሊጉ ዋንጫ ይፎካከራሉ የሚል እምነት እንደሌለው ገልጿል።

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ድምቀት ከነበሩ ተጨዋቾች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰው የቀደሞው ታሪክ አይሽሬው ተጨዋች ቴሪ ኦንሪ ትናንት ምሽት መደፈኞቹ በኢንተር ሚላን በሻምፒዮንስ ሊጉ ከተሸነፉ በኋላ በሰጠው ሀሳብ ቡድኑ አሁን ላይ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

ተከታታይ ሽንፈት እያስተናገዱ የሚገኙት መደፈኞቹ ካለፉት ስድስት ጨዋታዎች በሶስቱ ተሸንፈው ፤ አንዱን አቻ ሲለያዩ ቀሪውን ሁለት ጨዋታ ደግሞ አሸንፈዋል፡፡

ከትናንት ምሽቱ የኢንተር ሚላን ሽንፈት በኋላ ሀሳቡን የሰጠው ቴሪ ኦንሪ “ አሁን ላይ ቡድኑ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ አይደለም ፤እውነት ለመናገር እያሳዩት ከሚገኘው ብቃት አንፃር ዘንድሮ ለፕርሚየር ሊጉ ዋንጫ ይፎካከራሉ የሚል እምነት የለኝም ‘ ሲል ተናግሯል፡፡

ቴሪ ኦንሪ አያይዞ እንዳለው “ እሁድ ከቼልሲ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ እንዴት እንደሚሆኑ መገመት ከባድ ነው “ ብሏል፡፡

አርሰናል ቀጣይ እሁድ ምሽት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወደ ምዕራብ ለንደን በመጓዝ በስታምፎርድ ብሪጅ ቼልሲን የሚገጥም ይሆናል፡፡

✍️ይገደብ አባይ

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *