ፖርቹጋላዊው የአምስት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአል ነስር ቤት ጫማውን እንደሚሰቅል ተነግሯል፡፡
በእግርኳስ ህይወቱ በአምስት የተለያዩ ሀገራት ሊጎች መጫወት የቻለው የ39 አመቱ ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሳኡዲ አሁንም መድመቁን እንደቀጠለ ይገኛል፡፡
ሮናልዶ ከአልናስር የእግር ኳስ አስተዳዳሪዎች ጋር በነበረው ቆይታ በክለቡ ደስተኛ እንደሆነ እና በዚሁ ክለብ ጫማውን መስቀል እንደሚፈልግ ነግሯቸዋል ተብሏል፡፡
ጫማውን ስለሚሰቅልበት ቀን የተጠየቀው ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ “ በቅርቡ ይመስለኛል ከሁለት ወይም ሶስት አመት በኋላ እግርኳስ አቆማለሁ “ ሲል መናገሩ ይታወሳል፡፡
በሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ነስር ቤት ያለው ኮንትራት በሚቀጥለው ክረምት የሚጠናቀቀው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቀጣይ ውሉን ያድሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
✍️ይገደብ አባይ