• Fri. Nov 20th, 2026

የአትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ቲሸርት ለጨረታ ሊቀርብ ነው !

Byadmin

Nov 9, 2024

ከ23 አመታት በፊት በመጀመሪያው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር ላይ የውድድሩ መስራች የሆነው አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ የሮጠበት የሩጫ ቲሸርት በጨረታ ሊቀርብ እንደሆነ ተነግሯል።

ይህ ጨረታ የሚቀርበው የፊታችን ቅዳሜ ከታላቁ ሩጫ ቀን በፊት እንደሆነ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አትሌት መልካሙ ተገኝ ለሀገሬ ቴሌቪዥን ገለጿል።

አትሌት መልካሙ እንደሚለው ሀይሌ የሮጠበት ቲሸርት ለጨረታ የቀረበበት ምክንያት ለፌዴሬሸኑ ድጋፍ ለማድረግ በማሰብ ነው ብሏል።

በ1994 ዓ.ም የተጀመረውን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ማሸነፉ ይታወሳል።

23ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የፊታችን እሁድ ህዳር 08 በ50 ሺህ ተሳታፊዎች የሚካሄድ ይሆናል።

✍️ይገደብ አባይ

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *