ላለፋት 28 አመታት አብረው ሲሰሩ የነበሩት የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የሞሀ የመጠጦች ኢንዱስትሪ ድጋሜ ውላቸው አስረዋል።
ዛሬ በተደረገው በዚህ ስምምነት የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አትሌት መልካሙ ተገኝ፣ እና የሞሀ የመጠጦች ኢንዱስትሪ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ንጉስ ሰለሞን፣ሻምበል እሸቱ ቱራ፣አትሌት እልፍነሽ አለሙ፣አትሌት ቁጥሬ ዱለቻ እንዲሁም ሌሎች የስፖርቱ ዘርፍ አካላት ተገኝተዋል።
ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የሞሀ መጠጦች ኢንዱስትሪ በጥምረት ሲሰሩ መቆየታቸው የሚታወስ ነው።
ዛሬ ደግሞ እነዚህ ሁለት ተቋማት ለሚቀጥሉት 12 ወራቶች የአጋርነት ውላቸውን ያስቀጠሉ ሲሆን በዚህም ፔፕሲ ለፌዴሬሽኑ 4 ሚሊዮን ብር እና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለማበርከት ተስማምተዋል።
ይገደብ አባይ