• Fri. Nov 20th, 2026

ሳምንቱን በስፖርት

Byadmin

Nov 18, 2024

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ️ “ማንቸስተር ዩናይትድ የእኔን አስፈላጊነት አንድ ቀን ይረዳሉ::” ሲሉ ተናግሯል

ቡካዮ ሳካ እና አንቶኒዮ ሩዲገር በቢግሶ ፋውንዴሽን በኩል በሩዋንዳ ሴራሊዮን ኬንያ እና ታንዛኒያ ለሚገኙ ከ3,000 በላይ ህፃናት የገንዘብ እርዳታ አድርገዋል።

“ሊቨርፑል አይመቸኝም ቆሻሻ ክለብ ነው የርገን ክሎፕም ቆሻሻ ነው” እያለ የተሳደበው የእንግሊዝ ፕርምየር ሊግ ዳኛ ዴቪድ ኩት የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ዴቪድ ኩት ከፕሪሚየር ሊግ እና ኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎችን እንዳይመራ ውሳኔ አስተላልፏል።

” ፕሪሚየር ሊጉ አግዶክ ከቀረ ና እኛ ጋር በጥሩ ክፍያ በነፃነት ትሰራለህ ሲሉ የሳውዲ ፕሮ ሊግ የዳኞች ኮሚቴ ለ ዴቪድ ኩት ጥሪ አቅርበውለታል።”

ጋሪ ኔቭል አርሰናል ወቅታዊ አቋሙ ጥሩ ባይሆንም አሁንም ቢሆን ሃሳቡን እንዳልቀየረ በመግለፅ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን በዚ አመት አርሰናሎች እንደሚያሳኩ ገልጿል ።

🎙ሞሀመድ ሳላህ “የሊቨርፑል ደጋፊዎች ከጄራርድ ቀጥሎ የምንጊዜም ምርጡ ተጫዋቻቸው አድርገው እንዲያስታውሱኝ እፈልጋለሁ”

ፒየር-ኤሜሪክ ኦባሚያንግ: “በእግር ኳስ ተጫዋችነ ዘመኔ አንድ ማይረሳ ጊዜ መምረጥ ካለብኝ በባርሳ ውስጥ የነበረኝን ጊዜ እመርጣለሁ… ለዘላለም ማስታወስ የምፈልጋቸው ብዙ ጊዜዎች አሉ ነገር ግን ከሁሉም በላይ የባርሴሎና ደጋፊዎች ለኔ የነበራቸውን ፍቅር እመርጣለሁ”

ሩበን አሞሪም ለማንችስተር ዩናይትድ ቦርድ ክርስቲያን ኤሪክሰን፣ ካሴሚሮ፣ አንቶኒ እና ቪክቶር ሊንደሎፍ በእቅዳቸው ውስጥ እንደሌሉ ተናግሯል ሲል BBC ስፖርት ዘግቧል።

ከቼልሲ ጋር ምን ማሳካት ትፈልጋለህ?
🗣 ኮል ፓልመር: “ዋንጫዎችን ማሸነፍ እና ባላንዶርን ማሸነፍ እፈልጋለሁ”

ቫን ባስተን :-” ኢንግሊዝ ውስጥ ካሉ ቡድኖች አርሰናል ውቡ ክለብ ነው”

አንጄል ዲ ማሪያ በ2022 የአለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ ስለ ኤሚ ማርቲኔዝ በመጨረሻው ደቂቃ ያዳነበትን ሁኔታ ሲጠየቅ:-
“በጭራሽ ማሰብ አልፈልግም ፎቶውንም ማየት አልፈልግም ፈጣሪ እንዳተረፈን ነው ምቆጥረው::”

ዊልያን ሳሊባ የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ የሚያቀርብለት ከሆነ ማድሪድን ለመቀላቀል ፍላጎት አለው🇫🇷 ሎስ ብላንኮሶቹ የአርሰናሉን ተከላካይ ለማስፈረም እያሰቡ ነው ሲል Le10Sport ዘግቧል።

ናቾ ፈርናንዴዝ ስለ ሳውዲ ሊግ: “መዋሸት አያስፈልገኝም ግልፅ ነው እኔ እዚህ ሪያል ማድሪድ ውስጥ አገኝ ከነበረው የበለጠ ብዙ ገንዘብ አገኛለሁ… እዚህ የመጣሁት ለገንዘብ ብዬ ነው”

ፔፕ በሲቲ ቤት ለተጨማሪ ዓመት የሚያቆየውን ኮንትራት ለመፈራረም ከስምምነት መድረሱን ለክለቡ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ዘግበዋል።

አርሰናል ለዌስትሃሙ ተጫዋች መሀመድ ኩዱስ 100 ሚልየን ዩሮ ለማውጣት ተዘጋጅተዋል የ24 አመቱ ጋናዊ ተጫዋች መድፈኞቹን በመቀላቀል ከእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ውጪ በአውሮፓ እግር ኳስ መጫወት ይፈልጋል።

ፖል ፖግባ ከጁቬንቱስ ጋር ያለውን ኮንትራት በጋራ ስምምነት አቋርጠዋል።

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ58 ዓመቱ አንጋፋ ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ከአሜሪካዊው ወጣት ቦክሰኛ እና ዩቱበር ጃክ ፖል ጋር ያደረገው ቡጢ 79 ለ 73 በሆነ ድምር ውጤት ተሸንፏል።

ውድድሩ በበርካቶች ዘንድ ይጠበቅ እንጂ በሜዳ ላይ ብዙም ሳቢ ያልነበረ ፉክክር የታየበት ነበር። አሸናፊው ፓል 40 ሚሊዮን ዶላር ከ19 አመት በኋላ ወደ ቦክስ የተመለሰው ተሸናፊው ታይሰን ደግሞ 20 ሚሊዮን ዶላር ተሸልሟል።

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *