ጂያንሉይጂ ዶናሩማ ወይም ጂጂ ተብሎ የሚጠራው ኮኮብ በ 1999 ፌብሩዋሪ ወር 25ተኛው ቀን ላይ፣ በጣሊያን ደቡባዊ ክልል ከ ኔፕልስ በ ግራ የ ባህር ዳርቻ በኩል በካስተላማር ዲ ስታቢያ በምትባል ትንሽ ከተማ ተወለደ። አባት አልፎንሶ በመርከብ ላይ እንደ ረዳት ሆኖ ይሠራ ነበር፣ እናት ማሪኔላ ደግሞ የ ቤት እመቤት ነበረች። አልፎንሶ እና ወንድሙ አንቶኒዮ በ እግር ኳስ ፍቅር ያበዱ ሰዎች ነበሩ፣ ይህም ለ ጂጂ ቀድሞውኑ ለ እግር ኳስ ለየት ያለ እና የሚንቀለቀል ፍቅር እንዲኖረው አድርጎታል።
ከእሱ ቀድሞ ወንድሙ አንቶኒዮ የእግር ኳስ ተጫዋች ነበርና፣ ለ ጂጂ ትልቅ ማነቃቂያ ሆኖለታል።
ጂጂ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ግዙፍ ልጅ ነበር፣ በዚህም ምክንያት ጂጂዮ የሚል ቅፅል ስም እንዲያገኝ ሆኗል።
በ አንዳንድ ጨዋታዎች ላይ ተጋጣሚ ቡድኖች ሁሌ ከ እድሜው በላይ ነው ብለው ቅሬታ ባቀረቡ ቁጥር እናትየው ማሪኔላ የ ልደት ወረቀት ይዛ መታ ታሳያቸው ነበር። ጂጂ በቤታቸው አቅራቢያ ባለ ሜዳ ላይ ነበር በመጫወት የልጅነት ጊዜውን ያሳልፍ የነበረው። ከ 4 ዓመቱ ጀምሮ እግር ኳስን ይጫወት ነበር፣ ነገር ግን በ አካባቢው ወዳለ አካዳሚ የተቀላቀለው ዕድሜው 8 ዓመት በደረሰ ጊዜ ነበር። ወንድሙ አንቶኒዮ በ ኤሲ ሚላን የወጣቶች አካዳሚ ያለፈ ሲሆን፣ ጂጂም በተመሳሳይ መንገድ በ አካዳሚው ውስጥ ቦታውን አገኘ።
ጂጂ በ 14 ዓመቱ ትልቅ እርምጃን ተራምዷል። በ 2013ም በ ኤሲ ሚላን 250,000 ዩሮ የተቀበለ ሲሆን፣ ቤተሰቡ ሙሉ በሙሉ ሕይወታቸውን ከ ኔፕልስ ከተማ በ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደምትገኘው ሚላን ተዘዋውረዋል።
በመጀመሪያ ወራቶች በሚላን ለመኖር አስቸጋሪ ነበር፣ ነገር ግን ቤተሰቡ ቅርብ ስለነበረለት ብዙም አልከበደውም ነበር። በጨዋታዎች ላይም እየተገኙ ያበረቱት ነበር።
በ 2015 በ 16 ዓመቱ በ ሴሪ ኤ ላይ የመጀመሪያውን ጨዋታ በሚላን ተጫውቶ ታሪክ የፃፈ ሲሆን፣ ጁላይ 30 በ ቅድመ ውድድር ዘመን ጨዋታ ላይ ከ ሪያል ማድሪድ ጋር በነበረው ጨዋታ በ 72ኛው ደቂቃ ገብቶም ነበር የመጀመሪያ ጨዋታውን ማድረግ የጀመረው፣ ምንም እንኳን በ ፔናልቲ 10-9 የተሸነፈ ቢሆን Clean sheet ማስጠበቅም ችሎ ነበር።
ይህም ጨዋታ የ እሱን ተስፋ አነሳስቶ በ October 25 ከ ሳሱዎሎ ጋር በ ሴን ቲሮ ስታዲየም በ 16 ዓመት እና 242 ቀናት በሴሪ ኤ ታሪክ ውስጥ ሦስተኛው በ ዕድሜ ትንሹ ተጫዋች ለመባል በቅቷል። በጨዋታው ላይም ሚላን 2-1 በማሸነፍ ሙሉ 3 ነጥብ ወስዷል፣ በኋላም በሦስት ቀናት ውስጥ ሚላን 1-0 ባሸነፈበት ጨዋታ የመጀመሪያውን Clean sheet በ Serie A ላይ አስመዝግቧል። ይህን አካሄድ ያየውም በሰዓቱ የ ሚላን ግብ ጠባቂ የነበረው ሎፔዝ “የሚላን እና የጣሊያን እግር ኳስ የወደፊት ተስፋ” ብሎት ነበር።
በ 2016 የቋሚ ተሰላፊውን ቦታ በ እጁ አስገባ።
በተለይም 2016-17 ወቅት ፣ ጂጂ አስደማሚ ብቃቶችን አሳይቷል። በ August 21 ቶሪኖን 3-2 ሲያሸነፉ የመጀመሪያውን ፕሮፌሽናል ፔናልቲ የ አንድሪያ ቤሎቲን ኳስ በማምከን አስመዝግቧል፣ በ ዲሴምበር 23ም በ ሱፐርኮፓ ኢታሊያ የ ፍፃሜ ጨዋታ ከ ጁቬንቱስ ጋር በነበረው ጨዋታ መደበኛው ደቂቃ 1-1 ተጠናቆ በፔናልቲ 4-3 በማሸነፍ ዋንጫውን ከፍ አርገው አንስተዋል፣ በጨዋታው ያመከናት የ ፓውሎ ዲባላ ፔናልቲም በመላው የሚላን ማህበረሰብ ዘንድ አይረሴ ሆኖ ተቀምጧል።
በ 2017ም እስከ ጁላይ 11 ከ 2021 ድረስ የሚቆይ አዲስ ውል ተፈራርሞ በዓመት 6 ሚሊዮን ዩሮ ደሞዝ አግኝቷል። በዚያ ዓመት በአውሮፓ ዩኒቨርሲታ ክራዮቫን 1-0 በማሸነፍ የመጀመሪያውን የ አውሮፓ ጨዋታው ተጫውቷል፣ clean sheetም አስመዝግቧል። በ ዲሴምበር 30 ከ ፊዮረንቲና ጋር ተደርጎ 1-1 በሆነ ውጤት በተጠናቀቀ ጨዋታ የ 100ኛውን ጨዋታ ተጫውቷል፣ ይህም በሚላን ታሪክ ውስጥ ወጣቱ ተጫዋች ሆኖ ተመዝግቧል። በ April 15 ከ ናፖሊ ጋር በተደረገው ጨዋታ 100ኛውን የ ሴሪ ኤ ጨዋታ ተጫውቷል፣ በ19 ዓመት ከ 49 ቀናትም ሌላ record ሰብሯል። በፌብሩዋሪ 10 ከ ካግሊያሪ ጋር በነበረው ጨዋታ 3-0 በማሸነፍ የ 150ኛውን ጨዋታ አድርጓል።
በ 2021 ላይ ደግሞ በሴሪ ኤ የ ዓመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ እና በሴሪ ኤ Best 11 ስብስብ ውስጥ መካተት ችሎ ነበር። በ 2020-21 ወቅት በሴሪ ኤው ላይ አንድ ጨዋታ ብቻ አልፎት ሌላውን በሙሉ ተጫውቶ ሚላን ወደ ሁለተኛ ደረጃ በማምጣት ከ 2014 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቻምፒዮንስ ሊግን እንዲቀላቀሉ የራሱን አስተዋፅኦ አበረከተ። ነገር ግን በ 2021 ሜይ 26 የ ሚላን ዳይሬክተር ፓውሎ ማልዲኒ የ ፋይናንስ ችግር እንደደረሰባቸው አስታወቀ።
በ 2021 ጁን 16 ጂጂ ፒኤስጂን ተቀላቀለ፣ ይህም በአስቸጋሪ ውይይቶች እና ከ ከባባድ ድርድሮች በኋላ የተከተለ ነበር። በ ፒኤስጂ የመጀመሪያውን ጨዋታውንም በ 2021 ኦገስት 20 ነበር ያደረገው፣ እና በፍጥነት ከ ኬይለር ናቫስ ቀድሞ የመጀመሪያ ቋሚ ተሰላፊ ሆኖ ተሾመ።
በመጀመሪያ ዓመቱም በ 2021-22 የ ሊግ 1 ሻምፒዮንሺፕን አሸንፏል፣ እና በ 2022-23 እና 2023-24 ደግሞ ደጋግሞ አራት ጊዜ ተከታታይ ሻምፒዮንሺፕ አገኘ። በ 2022 እና 2024 ሁለት የኩፕ ደ ፍራንስ ሻምፒዮንሺፕን አሸንፏል። በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ላይ ደግሞ በ 2024-25 ወቅት ትልቅ ሚና ተጫወተ። በ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ላይ ከ ሊቨርፑል ጋር በተደረገው ጨዋታ፣ በፔናልቲ ሲለያዩ የ ዳርዊን ኑኔዝ እና የ ከርቲስ ጆንስን ፔናልቲዎች በማዳን ፒኤስጂን አሸናፊ በ ማድረግ ወደ ቀጣዩ ዙር እንዲያልፉ አስቻለ። የጎላ አስተዋፅኦ በማድረግም በአንድ የ ውድድር ዘመን ትሬብልን ባሸነፈው ባለ ታሪኩ PSG ውስጥ ዋና ተዋናይ ለመሆን በቃ። በ ፒኤስጂ ቤትም አራት ዓመታትን ከተጫወተ በኋላ በ 2025 ሴፕቴምበር 2 ላይ በ 26 ሚሊዮን ዩሮ ማንችስተር ሲቲን ተቀላቀለ፣ በ ፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ውስጥም በከፍተኛ ተስፋ ከተመ።
በ ብሔራዊ ቡድን ደረጃ ጂጂ በ 2016 የ ጣሊያን ብሔራዊ ቡድን ስብስብ አካል ሆነ፣ በአሁኑ ጊዜ ታዲያ የቡድኑ ካፒቴን ሆኖ ተሾሟል። በ 2017 የመጀመሪያውን ጨዋታውን ከ ሉቲኒያ ጋር ተጫውቷል፣ በ ዩሮ 2020 (2021) ውድድር ላይ በፋይናል ጨዋታው እንግሊዝ ላይ ፔናልቲ በማዳን ትልቅ ሚና ተጫወተ ጣሊያን የአውሮፓ ሻምፒዮን ሆነች ጂጂም የታሪኩ አንድ አካል ሆነ።
የ ጂጂ ታሪክ፣ ከትንሽ ከተማ እስከ ታላቅ ተፅኖ ፈጣሪነት የተሸጋገረው፣ እና ህልሙን አሳዶ ያገኘ ባለሙያ ታሪክ ነው። በማንችስተር ሲቲ አዲስ ምዕራፍ ሊጀምር ተዘጋጅቷል።