• Fri. Nov 20th, 2026

ታላቁ አፍራካዊ ሌጀንድ

ByAdmin

Sep 24, 2025

በአለማችን ዝነኛ የሆነው የፎርብስ መፅሄት በአንድ ወቅት አፍሪካዊ የሆኑ ዝነኛ እና ተፅእኖ በመፍጠር አቅም ያላቸው 40 ሰዎች ሲል ባወጣው ፅሁፉ 3ኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጠው ዲዲየር የቬስ ድሮግባ ቴቢሊይ በማርች 11 በፈረንጆቹ 1978 በአቢጃ ተወለደ ። በ1970ዎቹ አጋማሽ ሁለት ወጣት የባንክ ቤት ሰራተኞች ፍቅር ውስጥ በመግባት አንድ ላይ መኖር ጀመሩ ። ከጥቂት አመታት ቡሃላ እነኚ ሁለት ወጣት አይቮሪኮስታውያን ዲዲየር ድሮግባ የሚባልን ልጅ ወለዱ ። ዲዲየር ድሮግባ በዛው በትውልድ ከተማው እድገቱን አደረገ ። አይቮሪኮስት በዛን ወቅት የኢኮኖሚ ችግር ውስጥ መግባቷን ተከትሎ ብዙ አይቮሪያኖች ወደ ፈረንሳይ ስደትን በብዛት ማድረግ ጀመሩ ። በጊዜ ሂደት ድሮግባ እና ቤተሰቡ ችግሩ ከደረሰባቸው ዜጎች መካከል መሆናቸው አልቀረም ፤ ነገር ግን በወቅቱ በፈረንሳይ ሁለተኛ ዲቪዚየን የሚጫወተው የድሮግባ አጎት ሚሼል ጎባ ድሮግባ እና ቤተሰቡን በኢኮኖሚ ይረዳቸው ጀመር ። ማይክል ጎባ ፈረንሳይ ብዙ አፍሪካዊ ዜጎችን ወደ ሀገሯ ባስገባችበት ወቅት ወደ ፈረንሳይ ያቀና ሲሆን ፈረንሳይም አቅንቶ ለስታድ ብሪስቶኢስ መጫወት ችሏል። የድሮግባ ቤተሰቦች ከማይክል ጎባ የሚላክላቸውን ገንዘብ ከመጠበቅ ባሻገር አጎትዬው ወደ አይቮሪኮስት በመምጣት ልጃቸውን ዲዲየር ድሮግባን ወደ ፈረንሳይ አብሮት እንደሚያወስደው ወስነው ነበር። ነገር ግን በወቅቱ የድሮግባ አጎት ወደ አይቮሪኮስት እንዳይመለስ በፈረንሳይ መንገስት ከቪዛ ጋር በተገናኘ እገዳ ተጣለበት። በዛን ወቅት ነበር ቤተሰቡ በአጎቱ ሙሉ ወጪ ወደ ፈረንሳይ ከአጎቱ ጋር ሊሄድ የነበረውን ድሮግባን አጎቱ በፓሪስ እንዲጠብቀውና ለብቻው ወደ ፈረንሳይ እንዲጓዝ የወሰኑት።

በዚን ጊዜ ድሮግባ ወደ ፈረንሳይ መሄድ በጣም ፈርቶ ነበር ምክንያቱም ድሮግባ በወቅቱ የ5 አመት ልጅ የነበረ ሲሆን በፕሌን ሲሄድም የመጀመሪያው ነበር። ድሮግባ በ5 አመቱ የመጀመሪያ ጉዞውን ወደ ፈረንሳይ ከማያውቃቸው ሌሎች ሰዎች ጋር አድርጎ ፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ መድረስ ቻለ። በፓሪስ ቻርለስ ዲ ጋዩሌ ኤርፖርት በሰላም የደረሰው ዲዲየር አጎቱን በኤርፖርት ውስጥ አገኘው። ድሮግባ ወደ ፈረንሳይ ከሄደ ቡሃላ ቤተሰቦቹ በልጃቸው ላይ አንድ ተስፋ ነበራቸው ያም በትምህርቱ ላይ ሙሉ ትኩረቱን አድርጎ በትምህርቱ ትልቅን ደረጃ እንዲደርስ ነበር። በተቃራኒው አጎቱ ዲዲየር ድሮግባን ኳስ ተጫዋች የማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት ነበረው። በዚህም የተነሳ የዲዲየር ወላጆች እና አጎቱ በፍላጎታቸው ላይ በተደጋጋሚ ይጋጩ እና ይጣሉ ነበር ። በመጨረሻም ከብዙ ጥሎች ቡሃላ ዲዲየር ድሮግባ ትምህርቱንም ኳሱንም ጎን ለጎን እንዲያስኬድ ተስማሙ።

ድሮግባ በፈረንሳይ ለሶስት አመታት መጥፎ ጊዜን አሳለፈ ፤ ድሮግባ በአንድ ወቅት በኢንተርቪዉ ሲናገር ”በየቀኑ ያለቅስ እንደነበር እና ቤተሰቦቹም በከፍተኛ ደረጃ ይናፍቁት እንደነበር ወደ ሀገሩም መመለስ እንደሚፈልግ ለአጎቱ በተደጋጋሚ እንደነገረው ገልጿል።በወቅቱ በሁኔታውም የተናደደው አጎቱ ድሮግባን ወደ አይቮሪኮስት መልሶ ላከው ፤ ድሮግባ ወደ ቤተሰቦቹ ሲመለስ ነገሮች የበለጠ የከፉ ሆነው ጠበቁት ። ቤተሰቦቹ ድሮግባን ወደ ትምህርት ቢመልሱትም ብዙም ሳይቆይ የትምህር ቤት ክፍያ መክፈል የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደረሱ። የከፋ የሀገሪቷ ሁኔታ ችግሩን ያባባሰባቸው የድሮግባ ቤተሰቦች ልጃቸው ሰፈር ከመዋል ሌላ ምንም ማድረግ ሳይችሉ ቀሩ ፤ በዚህም ድሮግባ ለሶስት አመታት ሰፈር ውስጥ ከመዋል ባሻገር እግር ኳስን ከጓደኞቹ ከ8 አመቱ እስከ 11 አመቱ ድረስ መጫወት ቻለ።

By Admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *