መላው ቤተሰቡ የታላቁ ክለብ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ነበሩ ፤ ሁለት እህቶቹን ጨምሮ እናቱም አባቱም የማን ዩናይትድ የታወቁ ደጋፊዎች ነበሩ ።
ቤካም አባት እና እናቱ በትውልድ ከተማው ለንደን በ1969 የተጋቡ ሲሆን የቤቱ ብቸኛ ወንድ ልጅ እና የቤቱ ሁለተኛ ልጃቸው ዴቪድ ሮቤርት ቤካምን ከ6 አመታት የጋብቻ ቆይታ ቡሃላ በሜይ ሁለት 1975 ማግኘት ችለዋል ። አባት ዴቪድ ኤድዋርድ የማንችስተር ዩናይትዱ ኮከብ ሰር ቦቢ ቻርልተን የልብ ወዳጅ መሆናቸውን ተከትሎ ለቤካም ሙሉ ስም መሃል ላይ ሮቤርት የሚለውን መጠሪያ ለክብሩ ሲሉ አካተውለታል ። ለቤቱ ብቸኛ ወንድ ልጅ የሆነው ቤካም ከቤተሰቡ የማንችስተር ዩናይትድን ፍቅር ከልጅነቱም ወረሰ ፤ ቤካም ለማንችስተር ከነበረው ፍቅር የተነሳ ከልጅነቱ ኳስ ግጥሚያዎችን መከታተል ከዛም አልፎ ገና በቲኒሽ እድሜው በፓርኮች ውስጥ የኳስ ግጥሚያዎችን ማድረግ ጀመረ ። ቤካም በ2007 በሰጠው ኢንተር ቪዉ ልጅ እያለ ትምህርት ቤት አስተማሪው ስታድግ ምን መሆን ትፈልጋለህ ሲል ለጠየቀው ጥያቄ ”ኳስ ተጫዋች” ሲል ይመልስለታል ፤ መምህሩም አይ የምር ወደፊት ምንድነው የመሆን ፍላጎትህ ሲለው ቤካም ደግሞ ደጋግሞ ኳስ ተጫዋች መሆን ህልሙ መሆኑን እንደገለፀለት ይፋ አድርጓል ። የቤካም እናት ወላጅ አባት ማለትም የቤካም አያት አይሁዳዊ መሆኑን ተከትሎ ቤተሰቦቹም የአይሁዳውያን ቤተክርስቲያን በየ ሳምንቱ ካልሄደ ኳስ መጫወት እንደማይችል ይነግሩት ነበር ። በዚህም ቤካም ከልጅነቱ ከኳሱ በተጨማሪ ሃይማኖቱም ላይ በሰፊው ትኩረትን ሰጥቶ እንዲያድግ አድርጎታል ። ወላጆቹ ማን ዩናይትድ በኦልድትራፎርድ ጨዋታ ሲኖረው 320 ኪሎ ሜትሮችን አቋርጠው ጨዋታውን ለመመልከት ይሄዱ ነበር ። እናቱም አባቱም ለታላቁ ክለብ የተለየ ፍቅር ነበራቸው ። ቤካም የመጀመሪያ ሙከራውን በ12 አመቱ አካባቢ በቶትንሃም ቀጥሎ ብሪምስዳውን ሮቨርስ ወጣት ቡድን ማድረግ ቻለ ። ቤካም ብዙም ሳይቆይ ከተወሰኑ አመታቶች ቡሃላ ሪያን ጊግስ ፣ ጋሪ ኔቭል እና ፊል ኔቭል ፣ ኒኪ በት እና ፖል ስኮልስን በሚያሰለጥነው በኤሪክ ሃሪሰን የማንችስተር ወጣት ቡድንን መቀላለቀል ቻለ ።
ቤካም ቡድኑን በተቀላቀለበት አመት በ1992 በሜይ የወጣት ቡድኑ በደርሶ መልስ ጨዋታ ዋንጫ እንዲያሸንፍ ከፍተኛ ሚና መወጣቱን ተከትሎ በሴፕቴምበር 1992 በዋናው ቡድን ጥሪ ተደረገለት ። በጃንዋሪ 23 1993 ቤካም ፕሮፌሽናል ፊርማውን ለማን ዩናይትድ አኖረ ፤ ቤካም ብዙም ሳይቆይ ወደ ፕሪስቶን በውሰት ውል አመራ ። በፕሪስቶን 1994-95 የውድድር አመትን ብዙ ልምዶችን አካብቶ ወደ ዩናይትድ በድጋሚ ተመለሰ። ከዛን ጊዜ አንስቶ ቤካም በዩናይትድ ቤት መድመቅ ቻለ ። ለአመታት ድንቅ አቋምን ከማሳየት አልፎ በ1996-97 የውድድር አመት የፕሮፌሽናል ፉትቦል አሶሴሽን የአመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች በመባል ተሸለመ ። ቤካም ይሄኔ ነበር በቀጣዩ የውድድር አመት ጂዮርጅ ቤስት እና ኤሪክ ካንቱናን የመሳሰሉ ኮከቦች የለበሱትን የ7 ቁጥር መለያን በዩናይትድ ቤት እንዲለብስ የተደረገው ። በ2000ዎቹ ከፈርጊ ጋር አለመስማማቶች ከመፈጠራቸው አስቀድሞ ቤካም በክለቡ ሶስትዮሽ ዋንጫን ጨምሮ ብዙ ስኬቶችን አሸነፈ ።
ዴቪድ ቤካም የፈረንጆቹ ሚሊኒየም ሊገባ 5 ወራቶች ሲቀሩ ከውቅቱ ዝነኛ ዘፋኝዋ ቪክቶሪያ ጋር ትዳሩን መሰረተ ፤ በትዳር ህይወቱን መግፋት የጀመረው ቤካም ብዙም ሳይቆይ ከፈርጊ ጋር አለመግባባቶች መፈጠር ጀመሩ ።ቤካም ትሬኒንግ ላይ አለመገኘትን ጨምሮ ሌሎችም ጉዳዮች ከፈርጊ ጋር ያጋጩት ጀመር ፤ ከሁለት አመታት ቡሃላ ማለትም በ2002 የቤካም አባት እና እናት ትዳራቸውን ከ33 አመታት ቡሃላ በስምምነት አፈረሱ ። ቤካም የእናት እና የአባቱ የትዳር መፍረስ ብስጭት በተጨማሪም በአፕሪል ወር አስከፊ ጉዳትን በቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ከዲፖርቲቮ ላካሩኛ ጋር ሲጫወት አስተናገደ ። ቤካም የውድድር አመቱንም በጉዳት እንደማይጫወት ተነገረ ። ቤካም ብዙም ሳይቆይ በሜይ ወር ላይ በዩናይትድ የሚያቆየውን ሶስት አመታት ፈረመ ፤ ነገር ግን ከ6 ወራቶች ቡሃላ ከዩናይትድ የምታለያየው አጋጣሚ ተፈጠረች ። ፌብሩዋሪ 15 2003 ዩናይትድ ከ አርሰናል በኤፍኤ ካፕ ተገናኙ ፤ በጨዋታው ዩናይቶዶች ብዙ ኳሶችን አምክነው 2-0 ተሸነፉ ። በውጤቱ ፈርጊ ክፉኛ ተበሳጩ በዚህም መልበሻ ክፍል ተጫዋቾቻቸውን በሚያናግሩ ጊዜ ተናደው በወረወሩት ድንገተኛ ታኬታ ቤካም አይኑ አካባቢ ጉዳት አስተናገደ…በወቅቱ ታዋቂ አቋማሪ ድርጅቶች ፈርጊ ወይስ ቤካም በዚ አመት ማን ቀድሞ ክለቡን ይለቃል ሲሉ የቁማር ማስያዣ ርእስ አደረጓቸው ። እንዳሉትም ከሁለት አንዳቸው መልቀቃቸው አልቀረም ፤ ቤካም ከ394 ጨዋታዎች ቡሃላ 12 ዋንጫ ካሸነፈበት ከሚወደው ከልጅነቱ ክለብ በመልቀቅ ወደ ሌላኛው ታላቁ የአለማችን ክለብ ሪያል ማድሪድ በክረምቱ አመራ ። በዚህን ጊዜ ነበር አባቱ ቤካምን ከሚወደው ዩናይትድ መልቀቁን ከኤጀንቱ ሲሰማ ከፍተኛ ንዴት ውስጥ በመግባት ፈርጊን ከዳተኛ በሚል የወቀሰው ። በዚህም ቤካም ከፍተኛ ሃፍረት ተሰማው ቤካም አባቱ ከእናቱ ጋር ከተለያየ ቡሃላ ግንኙነታቸው ከመቀነሱ ባለፈ ዝውውሩን በመቃወም በፈርጊ ላይ ባደረገው ነገር የተነሳ ወደ ማድሪድ ሲያቀና የቤተሰብ ፎቶ ፕሮግራም ላይ አባቱን ሳይጠራው ቀረ ። አባቱም በድርጊቱ እንዳዘነ እና የቤተሰብ ፎቶ ግብዣው ላይ ባለመጠራቱ በጣም ማዘኑን ገልጿል ። ቤካም የሪያል ማድሪድ የጋላክቲኮ አንድ አካል ሆኖ ወደ ስፔን ካቀና ቡሃላ በማድሪድ አራት አመታትን አሳለፈ።
ቤካም በማድሪድ 2005-06 የአመቱ የሪያል ማድሪድ ምርጡ ተጫዋች መባል ቻለ ፤ እንግሊዛዊው ኮከብ በማድሪድ እንደ ቡድን ሁለት ዋንጫዎችን አሸነፈ ፤ በመጨረሻም ከ159 ጨዋታዎች ቡሃላ ማድሪድን በመልቀቅ ወደ አሜሪካ ከአሜሪካ ወደ ኤስ ሚላን ከሚላን ወደ ፔዤ አቀና ። ቤካም ምንም እንኳን ለሀገሩ እንግሊዝ Tournoi de france ዋንጫን ብቻ በ1997 ቢያሸንፍም ለእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አምበል በመሆን ከዛም ባለፈ ለሀገሩ ብዙ ከለፉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ መሆን ችሏል ። ታላቁ ተጫዋች በክለብ ደረጃ የመጨረሻ ፊርማውን ለፒኤስጂ የ5 ወራት ኮንትራት ሲፈራረም የ5 ወር ሙሉ ደሞዙን ለእርዳታ ድርጅት በመስጠት ነበር ። የአራት ልጆች አባት የሆነው ዴቪድ ቤካም በ2014 የራሱን ክለብ ኢንተር ማያሚን በባለቤትነት መያዝ ከቻለ ቡሃላ ከጥቂት ወራቶች ቡሃላ የዴቪድ ቤካም ዩኒሴፍ ፈንድ በሚል ህፃናቶች ላይ እርዳታ የሚሰራ ዝነኛ የህፃናቶች እርዳታ ድርጅት ማቋቋም ችሏል።
ቤካም ንቅሳቶችን የሚወድ ተጫዋች ሲሆን ከ65 በላይ ንቅሳቶች በሰውነቱ ላይ ተነቅሷል ። ከተነቀሳቸው መካከል 1999 የዩናይትድን የውድድር አመት በማስመልከት 99 እና የሚስቱን ስም ፣ በተጨማሪም የልጆቹ ስም ይገኙበታል ።ቤካም የ ornithophobia ተጠቂ ሲሆን ይሄም ከፍተኛ ወፎችን የመፍራት ፎቢያ ይባላል ። እንግሊዛዊው ኮከብ ልጁ ብሩክሊን እንደሱ ኳስ ተጫዋች ለመሆን በአርሰናል አካዳሚ የተጫወተ ሲሆን ኋላ ላይ ግን እንዳልቀጠለበት ተነግሯል ። ለዚህም ምክንያት ”ብዙ ሰዎች የቤካም ልጅ እያሉ እሱን ከአባቱ ጋር በማነፃፀራቸው እና ተፅእኖው ከፍ ያለ በመሆኑ እንደሆነ ቤካም በኢንተርቪዉ ገልጿል ። ሌሎች ቀሪ ሁለት ልጆቹ ደሞ ሞዴሊንግ ላይ በመስራት ላይ ይገኛሉ ። ቤካም ከ1990 ዎቹ ጀምሮ እስከ አሁንም ድረስ በእግር ኳስ ፣ በሞዴሊንግ ፣ በበጎ አድራጎትም ከራሱ አልፎ ሀገሩን ማስጠራት የቻለ ታላቅ ተጫዋች ነው ። እኛም ከታላላቅ እግር ኳስ ሌጀንዶች መካከል አንዱ የሆነውን የዴቪድ ቤካምን የህይወት ታሪክ የዳሰሰንበት ፕሮግራማችን ይህን ይመስል ነበር ሰላም !