ጥቅምት 8
ክሪስታል ፓላስ እንግሊዛዊውን ተከላካይ ማርክ ጉሂን በጥር ወር ለመሸጥ አቅደዋል።ሊቨርፑል የ25 አመቱን ተጫዋች ለማስፈረም ግንባር ቀደም ፈላጊ ክለብ አይደሉም። ባርሴሎና፣ሪያል ማድሪድ እና ባየር ሙኒክ የተጫዋቹ ፈላጊዎች ናቸው።
ቶተንሃም እና ሊቨርፑል ጋናዊውን የበርንማውዝ የክንፍ መስመር ተጫዋች አንቶኒ ሴሜንዮ ለማስፈረም ይፈልጋሉ።
ኢንተር ሚላን ብራዚላዊውን ኮከብ ኔይማር ጁኒየርን በጥር ወር ለማስፈረም ተዘጋጅተዋል እየተባለ ያለውን ወሬ አጣጥሏል።
የማንቸስተር ዩናይትዱ አለቃ ሩበን አሞሪም የኢንተር ሚላኑን ግራ መስመር ተከላካይ ፌዴሪኮ ዲማርኮ ፈላጊ ነው ነገርግን ተጫዋቹ ለጊዜው በሳንሲሮ የመቆየት ፍላጎት አለው።
የባርሴሎናው ግብ ጠባቂ ማርክ አንድሬ ቴር ስቴገን በጥር ወር በክለቡ ይቆይ ወይስ ይለቃል የሚለው እስካሁን ከውሳኔ አልደረሰም።
ኮል ፓልመር በጉዳት ምክንያት ለተጨማሪ 6 ሳምንታት ከሜዳ ርቆ ይቆያል ሲል አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ተናግሯል።
ክሪስትያኖ ሮናልዶ ሃገሩን ከየትኛውም ተጨዋች በላይ የወከለ ተጨዋች ነው ለእኔ ከእርሱ ጋር አብሮ መጫወት ዕድል ነበር … ሮናልዶን በቅርበት ሆኜ መመልከቴ እንዴት አንድ ተጨዋች ለረጅም አመታት በከፍተኛ ደረጃ በምርጥነት መጫወት እንደሚችል ተምሬያለው ። ሲል ማርከስ ራሽፎርድ ተናግሯል
አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ ከ ዛሬው የፉልሀም ጨዋታ በፊት የሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ…
የሊጉ መሪ አርሰናል በ8ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሜዳው ውጭ ከፉልሀም ይጫወታል።
ስፔናዊው አሰልጣኝ ዛሬ የሚደረገውን ጨዋታ በተመለከተ ስለ ተጨዋቾች ጉዳት እና ተያያዥ ጉዳዮች መግለጫ ሰጥቷል።
👉ስለ ማርቲን ኦዴጋርድ:- ከዌስትሀም ዩናይትድ በነበረው ጨዋታ ጉዳት የገጠመው ማርቲን ኦዴጋርድ ገና ልምምድ እንዳልጀመረ ተናግሯል። አምበሉ ከቀጣዩ ኢንተርናሽናል ረፍት በኋላ ወደ ሜዳ ይመለሳል ተብሎ እንደሚጠበቅም ሚካኤል አርቴታ አሳውቋል።
👉ማርቲን ዙቢሜንድ:- ከሀገሩ ስፔን ጋር ሁለት ጨዋታዎችን በማድረጉ ምክንያት ልምምድ እንዳልሰራ እና ረፍት ተሰጥቶት እንደነበር ገልጿል። አማካዩ ትላንት ልምምድ ባይሰራም ለለንደን ደርቢው ጨዋታ ዝግጁ መሆኑን ይፋ አድርጓል።
👉ፒሮ ሂንካፒ:- ጉዳት ላይ የነበረው ኢኳዶራዊው ተከላካይ ልምምድ የጀመረ ሲሆን ምን አልባትም በነገው ጨዋታ ዕድል ሊያገኝ እንደሚችልም ይፋ ተደገርጓል።
👉ቪክቶር ዮኬሬስ:- አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ በስዊዲናዊው አጥዊ ብቃት ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል። ብዙ ጨዋታዎች ላይ ግብ ላያስቆጥር ይችላል ነገር ግን እሱ ይሄንን ጫና የመቋቋም አቅም እንዳለው አሰልጣኙ ገልጿል።
👉ኖኒ ማዱኬ እና ካይ ሀቨርዝ በጥሩ ሁኔታ እያገገሙ እንደሚገኙ እና በቅርቡ ወደ ሜዳ እንደሚመለሱ የገለጸው ሚካኤል አርቴታ ባለፉት ሁለት ዓመታት በክራቨን ኮቴጅ ፉልሀምን ማሸነፍ ባይችሉም ጠንከራ መሆናቸውን ለማሳየት ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ተናግሯል።
👉ከማርቲኔሊ የሚፈልገውን ነገር እያገኘ እንዳለ የተናገረው ስፔናዊው አሰልጣኝ በ10 ጨዋታ 3 ግብ ብቻ የተቆጠረበት የተከላካይ ክፍሉ ይበልጥ ጠንካራ መሆን ይጠበቅበታል ብሏል።
🎙 ጋብርኤል ማርቲኔሊ
“አርሰናል ለቶፕ ፎር ብቻ የሚታገል ቡድን አይደለም ፤ ለዋንጫው የሚፋለም ቡድን አንጂ ፤ ፕሪሚየር ሊጉን እና ቻምፒዮንስ ሊግን ማሸነፍ ለደጋፊው የሚገባው ነው።”
“አርቴታ ሁልጊዜ ለእኔ በጣም ጥሩ ነበር ባለፈው የውድድር አመት ብዙም ጥሩ ሳልጫወት እንኳን ወደ እሱ ቢሮ ሄጄ እድል እንዲሰጠኝ ስጠይቀው እሺ በርታ እንጂ ችግር የለውም ብሎ ቦታዬን አረጋግጦልኛል።”
“ያልኩት እንዲ ብቻ ነው “ሁሉንም ጨዋታ መጫወት ብቻ ነው የምፈልገው ታውቃለህ?” በውድድር ዓመቱ ብዙ ጨዋታዎች እንደነበሩን ተረድቻለሁ።”
“ይህን እድል ታዲያ ሳገኝ በጣም ደስተኛ ነኝ ነበርኩ የተሰጠኝን ዕምነት ሳልሰስት ለመስጠት እየጣርኩ ነው ፤ ይህንን ክለብ በእውነት እወደዋለሁ።” ብሏል
ዩኤፋ የፋይናንሺያል ፌር ፕሌይ ህግን በመጣስ ጁቬንቱስ ላይ ክስ ከፍቷል !
ጁቬ በዚህ የተነሳ ጉዳዩ እስኪጣራ እና ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የዝውውር እገዳ ሊጣልበት ይችላል ተብሏል ምክንያቱም ደሞ ባለፉት ሶስት የውድድር ዘመናት የፋይናንሺያል ፌር ፕሌይን ህግ አላከበሩም በሚል ተከሷል።
ዛሬ የሚደረጉ ተጠባቂ ጨዋታዎች
🏴በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ
08:30 | ኖቲንግሃም ከ ቼልሲ
11:00 | ብራይተን ከ ኒውካስትል
11:00 | በርንሌይ ከ ሊድስ
11:00 | ክሪስታል ፓላስ ከ በርንማውዝ
11:00 | ማን ሲቲ ከ ኤቨርተን
11:00 | ሰንደርላንድ ከ ወልቭስ
01:30 | ፉልሃም ከ አርሰናል
🇪🇸በስፔን ላሊጋ
12:15 | ባርሴሎና ከ ጂሮና
04:00 | አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ኦሳሱና
🇮🇹 በጣልያን ሴሪ ኤ
03:45 | ሮማ ከ ኢንተር ሚላን
🇩🇪በጀርመን ቡንደስሊጋ
12:30 | ባየር ሙኒክ ከ ዶርትሙንድ