• Fri. Nov 20th, 2026

ሳምንቱን በስፖርት

ByAdmin

Oct 19, 2025

ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለኢትዮጵያውያን መልእክቱን አስተላልፏል 

“ሰላም እንዴት ናቹ ኢትዮጵያዊያን ፤ ሳታቋርጡ ሰለምትደግፉን በጣም አመሰግናለሁ።”

ክሪስትያኖ ሮናልዶ ከ2010 የውድድር ዘመን አንስቶ  ያለፉትን 15 አመታት በወጥነት በአማካይ በአመት 50 ግቦችን እያስቆጠረ ተጫዉቷል 🤯

በዚህ የውድድር ዘመን ኦፕታ ሱፐር ኮሚፒዩተር በሲዝኑ መጨረሻ የሊጉን ዋንጫ የሚያሳካው ቡድን አርሰናል ነው በማለት ቅድመ ግምታቸውን አስቀምጠዋል ኦፕታ ለመድፈኞቹ 44% ሊጉን የማሳካት ዕድል አላቸው ከየትኛውም ክለብ በተሻለ መልኩ ብለዋል !

ኳታር የተባበሩት አረብ ኢምሬትስን 2 ለ 1 ባሸነፈችበት ጨዋታ ላይ በተፈጠረው ፀብ ደጋፊዎች ሲፈነካከቱበት የነበሩት……. 

ሌላው በጠርሙስ በወንበር በምን ይፈነካከታል እነዚህ በስልክ በመኪና ቁልፍ ነበር 😁

ፓውሎ ማልዲኒ 🗣 ከሜሲ ጋር በተቃራኒ ሆነን አልተጫወትንም……ምክንያቱም ሜሲ በወቅቱ ተጎድቶ ነበር ። ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን ተጎድቶ ነበር 👍

ጋዜጠኛው 🗣 ሜሲ እድለኛ ነበር ካንተ ጋር በተቃራኒ ባለመጫወቱ ።

🗣 አይ አይ እኔ ነበርኩ እድለኛው ብሏል 

ሞሮኮ ከ አፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ መጀመር በፊት በህዳር ወር ላይ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ከአርጀንቲና ጋር የታንጄር ስታዲየም ለመጫወት ጥያቄ አቅርበዋል !

የብ/ቡድኑ አሰልጣኝ ዋሊድ ጥሩ መፈተኛ እንደሚሆን በማሰብ ከአርጀንቲና ጋር የመጫወት ፍላጎት እንዳለቸው ቢገልፁም ደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር አርጀንቲና ግን ለወዳጅነት ጨዋታው 10 ሚሊየን ዶላር እንዲከፈላት ጠይቋለች ተብሏል።

ሊዮ ሜሲ “ሜሲ ካፕ” የተሰኘ አዲስ የታዳጊዎች ወድድር በግል መጀመሩን አስታውቋል !

ውድድሩም ከ16 ዓመት በታች በሆኑ ተጫዋቾች የሚደረግ ሲሆን የ ማንቸስተር ሲቲ ፣ ቼልሲ ፣ ባርሴሎና ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ ፣ ኢንተር ሚላን ፣ ኒው ኦልድ ቦይ ፣ ሪቨር ፕሌት እና ኢንተር ሚያሚ U16 ቡድን በወረሃ ዲሴምበር ሊደረግ በታቀደው አዲስ የሜሲ ሊግ ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

ጋዜጠኛ – ካሲላስ ወይስ አንተ?

የጋና ብሄራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ቤንጃሚን አሳሬ፡-

“ይህን ጥያቄ መጠየቅ እንኳን ተገቢ ነው ? አንተ ልክ ነው ብለህ ታስባለህ? እንዴት እኔን ከሌላ ጋር ታወዳድረኛለህ ?ምንም ጥያቄ የለውም እኮ ይሄ እርግጥ ነው እኔ ነኝ”

🗣 ሩበን አሞሪም ከራትክሊፍ ድጋፍ እንዳለው ሲጠየቅ ፦

“አዎ እሱ ሁል ጊዜ ይነግረኛል አንዳንድ ጊዜ መልእክት ይልክልኛሌ “በጣም አስፈላጊው ነገር የሚቀጥለው ጨዋታ ነው” ይለኛል ።

“ለእኔ የእሱን ድጋፉን ማግኘቴ በጣም ጥሩ ነው።.” ሲል ተናግሯል ።

የቀድሞ የሊቨርፑል አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ

በሊቨርፑል አሰልጣኝነቴ ወደ ቡድኔ ሳላስፈርመው ያለፈ የሚቆጨኝ ብቸኛው ተጨዋች ሶን ሂዩንግ ሚን ነው … ለሊቨርፑል የሚመጥን ብቃት ነበረው ።

ጋብሬል ማጋሌሽ ስለ ማክስ ዳውማን በስካይ ስፖርት ኔትወርክ ላይ የተናገረው

“ማክስ ዳውማን ልዩ ተሰጥኦ አለው፣ እንደ እሱ ያለ ነገር ከዚህ በፊት አይቼ አላውቅም፣ በዚህ ዕድሜው የሚያሳየው ተሰጦ ልዩ ነው፣ የ15 ዓመት ልጅ ብቻ፣ የማይታመን ነው።” 

ፊፋ ለ2026 የአለም ዋንጫ ከቅድመ ትኬት ሽያጭ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ትኬቶችን መሸጡን አስታውቋል።

ሊዮኔል ሜሲ በእግር ኳስ ታሪክ 4000 የተሳኩ ድሪብሎችን ያደረገ የመጀመሪያው እና ብቸኛ ተጫዋች ነው 

ጋዜጠኛ :- ኬቨን ዴብሮይን ወይስ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ?

ስኮት ማክቶሚናይ 🎙

“ሁለቱም አስደናቂ ተጫዋቾች ናቸው ለኔ ግን ቡሩኖ ሌላ ደረጃ ላይ ያለ ተጫዋች ነው”

ጋዜጠኛ :- ኬቨን ዴብሮይን ወይስ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ?

ስኮት ማክቶሚናይ 

“ሁለቱም አስደናቂ ተጫዋቾች ናቸው ለኔ ግን ቡሩኖ ሌላ ደረጃ ላይ ያለ ተጫዋች ነው”

የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ጁአን ላፖርታ 

እኔ ካቶሊክ ነኝ ፈጣሪ አለ ብዬም አስባለሁ ። ፈጣሪ ካለ የባርሴሎና ደጋፊ ነው ብዬ አስባለሁ 

By Admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *