ቼልሲዎች የ21 አመቱን ስፔናዊ አጥቂ ሳሙኤል ኦሞሮዲዮን በሚቀጥለው ክረምት ለማስፈረም ከ100ሚ ዩሮ በላይ ለማውጣት ተዘጋጅቷል
አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ከኢንተር ማያሚ ጋር አዲስ ኮንትራት ይፈራረማል ተብሎ እየተጠበቀ ይገኛል።
የባርሴሎና መልማዮች ማሰን ግሪንዉድ ለክለቡ ማርሴይ በሳምንቱ መጨረሻ አራት ጎሎችን ሲያስቆጥር በስታዲዮም በመገኘት ተመልክተዋል።
በ8ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱ ትልቅ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአንፊልድ በተደረገው ጨዋታ ብሪያን ምቤሞ እና ሃሪ ማጉዌር የዩናይትድን የአሸናፊነት ግቦች አስቆጥረዋል። ኮዲ ጋክፖ የሊቨርፑልን ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች ሆኗል።
የመርሲሳይዱ ክለብ በፕሪሚየር ሊጉ ብቻ ለ3ኛ ተከታታይ ጊዜ ሲሸነፍ በሁሉም ውድድሮች ደግሞ ለ4ኛ ተከታታይ ጊዜ የተሸነፈበት ሆኗል።
አሰልጣኝ ሩብን አሞሪም ማንችስተር ዩናይትድን ከተረከቡ በኋላ በፕሪሚየር ሊጉ ለመጀመርያ ጊዜ በተከታታይ ያሸነፉበት ሆኗል።
ቀያይ ሰይጣናቱ ከ2016 በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በአንፊልድ የምንጊዜም ተቀናቃኛቸውን አሸንፈዋል።
ሊቨርፑል በ15 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ከሊጉ መሪ አርሰናል ያለው የነጥብ ልዩነትም ወደ አራት ሰፍቷል።
ትላንት የተደረጉ የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ጨዋታዎች
🏴በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ
ቶተንሀም 1-2 አስቶን ቪላ
ሊቨርፑል 1-2 ማንችስተር ዩናይትድ
🇪🇸በስፔን ላሊጋ
አልቼ 0-0 አትሌቲክ ቢልባኦ
ሴልታ ቪጎ 1-1 ሪያል ሶሴዳድ
ሌቫንቴ 0-3 ራዮ ቫልካኖ
ጌታፌ 0-1 ሪያል ማድሪድ
🇮🇹 በጣልያን ሴሪ ኤ
ኮሞ 2-0 ጁቬንቱስ
ካግላሪ 0-2 ቦሎኛ
ጄኖአ 0-0 ፓርማ
አታላንታ 0-0 ላዚዮ
ኤሲ ሚላን 2-1 ፊዮረንትና
🇩🇪በጀርመን ቡንደስሊጋ
ፍራይበርግ 2-2 ፍራንክፈርት
ሴንት ፓውሊ 0-3 ሆፈናየም
🇫🇷በፈረንሳይ ሊግ 1
ሌንስ 2-1 ፓሪስ
ሎሬንት 3-3 ብረስት
ሬንስ 2-2 አክዥሬ
ቶሉስ 4-0 ሜትዝ
ናንትስ 0-2 ሊል