• Fri. Nov 20th, 2026

የአንድ ወጣት ግብ ጠባቂ አሰቃቂ ሞት !

ByAdmin

Oct 20, 2025

በሴኔጋል ዮምቦል ክልል ለግሪ ጎስት አካዳሚ የሚጫወተው ወጣቱ ግብ ጠባቂ ቼክ ቱሬ በሚያሳዝን ሁኔታ ተገድሏል።

ታሪኩ አንዳንድ ሰዎች ደውለው “እኛ የአንድ ትልቅ ክለብ ሀላፊዎች ነን፣ በቅርቡ ስካውቶቻችንን ልከን ስትጫወት አይተናል ብቃትህንም አየተን ወደነዋል እና  ልናስፈርምህ ስለፈለግን አሁኑኑ የህክምና ምርመራ ለማድረግ እና የኮንትራት ፊርማ ለማድረግ ወደ ጋና ና” ይሉታል

ቼክ ቱሬ አምኖ ያለውን ገንዘብ ሁላ ሰብስቦ ወደ ተጠራበት ቦታ ሄደ ነገር ግን እንደደረሰ ተታሎ እንደነበር እና ምንም አይነት ውል እንደሌለ ቢረዳም ገና እዛ ከምድረሱ መጀመሪያ ተደግሶለት በነበረው አጀብ መሰረት በርካታ ፈርጠም ያሉ ሰዎች አስገድደው መኪና ውስጥ አስገብተው ወደ አልታወቀ ቦታ ወሰዱት ….

ከዚያም ቤተሰቡ ጋር ደውለው “ልጃቹን ለማስፈታት ይህን ያህል ገንዘብ መላክ አለብቹ” ብለው ይናገሩል ነገር ግን ድሆች የነበሩት የቼክ ቱሬ ቤተሰቦች ገንዘቡን ማግኘት ባለመቻላቸው ምክንያት አጋቾቹ ወጣቱን ግብ ጠባቂ በአሰቃቂ ሁኔታ ገደሉት። 

አስከሬኑ በአሁኑ ጊዜ በጋና ዋና ከተማ አክራ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የዚህን የ18 አመት ወጣት ገዳዮችን ለማግኘት ፖሊስ ምርመራ ማድረግ መጀመሩን አስታውቋል ።

የሟች እናትም ዜናውን ስሰማ በድንጋጤ ራሷን እንደ ሳተች እና አሁንም ድረስ በሆስፒታል አስቸካይ ዕርዳታ ክፍል ውስጥ እንደምትገኝ እና እህቱም በመርዶው ምክንያት መረጋጋት እንዳልቻለች ተያይዞ ተገልጿል።

By Admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *