• Fri. Nov 20th, 2026

ጥቅምት 11 2018 አ/ም ማክሰኞ ማለዳ የወጡ አጫጭር ስፖርታዊ ዜናዎችን…..

ByAdmin

Oct 21, 2025

ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ የ25 አመቱን እንግሊዛዊ የመሀል ተከላካይ ማርክ ጉሂን ከክሪስታል ፓላስ ጋር ለማስፈረም በቅርበት እየተከታተሉት ነው። 

አርሰናል የጁሪየን ቲምበርን ኮንትራት ለማደስ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል

ግርሃም ፖተር የስዊድን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል !

የባሎንዶሩ አሸናፊ ኡስማን ዴምቤሌ ከጉዳት ተመልሷል ። በዚህ ሳምንት በሚደረገው የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታም ወደ ፒኤስጂ ስብስብ ተካቷል !

አትሌቲኮ ማድሪዶች አርሰናል ሙሉ ፋሲሊቲ አለሟላም በማለቱ አቤቱታውን ለ አውሮፓ እግር ኳስ ቅሬታውን አቅርቧል !

በቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ አርሰናልን ለመግጠም ለንደን የከተመው አትሌቲኮ ማድሪድ በአርሰናል ስታዲየም የፋሳሊቲ ሁኔታ ላይ ቅሬታ አሰምቷል

 የአትሌቲኮ ተጫዋቾች ልምምዳቸውን ካከናወኑ ቡሃላ ሻወር ለመውስድ ሲገቡ ሙቅ ውሃ ማግኘት አልቻሉም 

ወትሮ ለለባቸው ማጥፊያ ሙቁ ውሃን አዘውትረው የሚጠቀሙት የአትሌቲኮ ተጫዋቾች በሁኔታው እንደተበሳጩ እና ሻወር ሳይወስዱ በፍጥነት ስታዲየሙን ለቀው ወደ ሆቴል እንዳመሩ ተገልጿል።

ተጫዋቾቹ ያሰሙትን ተከትሎ ክለቡም ለUEFA አርሰናል በቂ አቅርቦት አልሰጠንም ሻወር የወስደነው ሆቴል ገብተን ነው ሲል አቤቱታውን አቅርቧል !

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ በወሳኝ ጨዋታዎች ይመለሳል!

አርሰናል በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በቻምፒየንስ ሊጉ ነገ ምሽት አትሌቲኮ ማድሪድን ይገጥማል ።

አርሰናል ከዚህ ቀደም ከአትሌቲኮ በቻምፒየንስ ሊጉ አንድም ጊዜ ያልተገናኘ ሲሆን በኢሮፓ ሊግ ሁለት ጨዋታዎችን አድርጎ በአንዱ ሽንፈትን በተቀረው አቻ ተለያይቷል ። 

🎙 ማይክል አርቴታ 

“ሁለታችንም ትልልቅ ክለቦች በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ያለፍን ነን ፤ ሲሞኔ ከአትሌቲኮ ጋር ያደረገው ነገር ድንቅ ነው ቡድኑ ሁል ጊዜ ትክክለኛ የማሸነፍ አላማ ያለው ነው።”

“ሲሞኒ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን የምማርበት ሰው ነው ፤ ስለ እሱ በጣም ጥሩው ነገር ልናገር ካልኩ ብዙ መጠቀስ እችላለው ግን ለኔ ጨዋታን ለማሸነፍ ያለው ፍላጎቱ የተለየ ነው።”

“ሲሞኔ ወደ ፕሪምየር ሊግ ከመጣ በእርግጠኝነት ሊጉ የበለጠ በጣም ከባድ ይሆናል ምክንያቱም ቀደም ሲልም በእንግሊዝ ውስጥ ብዙ ጥሩ አሰልጣኞች አሉ እና እሱም ሲጨመርበት የተለየ ይሆናል ግን ያንን ልምድ ማግኘት መፈለግ ወይም አለመፈለግ የሱ ጉዳይ ነው።” ብሏል

🇪🇺ዛሬ የሚደረጉ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች

01:45 | ባርሴሎና ከ ኦሎምፒያኮስ 

04:00 | አርሰናል ከ አትሌቲኮ ማድሪድ 

04:00 | ባየር ሌቨርኩሰን ከ ፒኤስጂ 

04:00 | ኮፐንሀገን ከ ዶርትሙንድ 

04:00 | ኒውካስትል ከ ቤኔፊካ 

04:00 | ፒኤስቪ ከ ናፖሊ 

04:00 | ሮያል ዩኒየን ከ ኢንተር ሚላን 

04:00 | ቪያሪያል ከ ማንችስተር ሲቲ

By Admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *