• Fri. Nov 20th, 2026

የሻምፒዮንስ ሊጉ ክስተት አስቶንቪላ

Byadmin

Oct 23, 2024

ከ41 አመታት በኋላ ወደ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የተመለሰው የእንግሊዙ ክለብ አስቶንቪላ በአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ድንቅ መሪነት የውድድሩ ክስተት መሆን ችሏል፡፡

ከሁለት አመት በፊት ከስፔኑ ክለብ ቪያሪያል ወደ አስቶንቪላ የተቀላቀሉት ስፔናዊው አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ በክለቡ ታሪክ አይሽሬ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

የዚህም ማሳያ የሆነው አሰልጣኙ ክለቡን በአያዙ ወራቶች ከታላላቆቹ ክለቦች ጋር ተፎካካሪ አድርገው እንዲሁም ከ41 አመታት በኋላ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እንዲሳተፍ አድረገውታል፡፡

ዘንድሮ በአዲስ ቅርጽ እና ፎርማት ውድድሩን እያደረገ የሚገኘው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሶስተኛውን ዙር እያካሄደ ይገኛል፡፡

የእንግሊዙ ክለብ አስቶንቪላ በዚህ ውድድር ባደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች ሶስቱንም በማሸነፍ ሙሉ ዘጠኝ ነጥብ ማግኘት ችሏል፡፡ይህም የውድድሩን የሁለተኛ መዕራፍ በበላይነት አጠናቋል፡፡

አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የሚመራው አሶንቪላ በቀዳሚነት የሲውዘርላንዱን ክለብ ያንግ ቦይስ፤የጀርመኑን ክለብ ባየር ሙኒክን እንዲሁም የጣሊያኑን ክለብ ቦሎኛን በማሸነፍ የውድድሩ ክስተት መሆን ችሏል፡፡

አስቶንቪላ ባደረጋቸው ያለፉት ሶስት ጨዋታዎች ስድስት ጎሎችን ሲያስቆጥር አንድም ጎል ደግሞ መረቡን ሳያስደፍር ወጥቷል፡፡

እንደ ክለቡ ሁሉ የውድድሩ ክስተት የሆነው ጆን ዱራን ባደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች ሁለት ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡
አስቶምቪላ በቀጣይ ከክለብ ብሩዥ እና ከጁቬንቱስ ጋር ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል፡፡

✍️ይገደብ አባይ

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *