ባርሴሎና በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ትናንት ምሽት በተጠባቂው ጨዋታ በሜዳው የባቫሪያኑን ክለብ ባየር ሙኒክ አስተናግዶ አራት ለአንድ በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
በውድድር ዘመኑ አስደናቂ ብቃትን እያስመለከተን የሚገኘው ብራዚላዊ ራፊንሀም በጨዋታው ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር ሀትሪክ መስራት ችሏል።
ራፊንሀ በያዝነው የውድድር ዘመን ከ13 ጨዋታዎች ዘጠነኛ ጎሉ ሆኖ ተመዝግቦለታል።
በላሊጋው በነሀሴ ወር ሪያል ቫላዶሊድ ላይ የሰራውን ጨምሮ ሁለተኛ ሀትሪኩንም በምሽቱ ግጥሚያ መስራት ችሏል።
ራፊንሀ በ 2022 የክረምቱ የዝውውር መስኮት ሊድስ ዩናይትድን በመልቀቅ በ55 ሚሊየን ፓወንድ የካታሎኑን ክለብ መቀላቀሉ ይታወሳል።
ብሉግራናዎቹ በአዲሱ አሰልጣኛቸው ሀንስ ፍሊክ ስር ድንቅ ጊዜን እያሳለፉ የሚገኝ ሲሆን የፊታችን ቅዳሜ በተጠባቂው የኤልክላሲኮ ግጥሚያ የምንግዜውም ተቀናቃኛቸውን ሪያል ማድሪድ በላሊጋው የሚገጥሙ ይሆናል።