የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የ2024-25 የውድድር ዘመን የሊግ ፎርማት ጨዋታዎች በትላንትናው እለትም ቀጥለው ሲደረጉ የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን ስፓርታ ፕራግን አምስት ለዜሮ በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የ2023 የመድረኩ አሸናፊዎች በ26 ጨዋታዎች ላይ ያለ ሽንፈት በውድድሩ መጓዝ መቻላቸውን ተከትሎም አዲስ ሪከርድን መዝግበዋል።
ኖርዌያዊው አጥቂ አርሊንግ ሀላንድ በበኩሉ በጨዋታው ሁለት ጎሎችን ከመረብ ማገናኘት የቻለ ሲሆን በአጠቃላይ በቻምፒየንስ ሊጉ ያስቆጠራቸውን የጎሎችን ብዛትም 44 አድርሷል።