• Fri. Nov 20th, 2026

“አስደናቂው ” ቪኒሺየስ ጁንየር

Byadmin

Oct 24, 2024

” ባሎንዶርን ያሸንፋል”

ብራዚላዊው ኮከብ ባሳለፍነው ማክሰኞ ሪያል ማድሪድ ከሁለት ለዜሮ መመራት ተነስቶ ቦሩሲያ ዶርትመንድን በቻምፒየንስ ሊጉ በሁለተኛው አጋማሽ በተቆጠሩ ጎሎች አምስት ለሁለት ሲያሸንፍ ሀትሪክ መስራት ችሏል።

የፊታችን ሰኞ በሚካሄደው የባሎንዶር ሽልማት የማሸነፍ ቅድሚያ ግምት የተሰጠው ተጫዋችም ነው።

ጣልያናዊው የሎስብላንኮዎቹ አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲ ከማክሰኞው ድል በኋላ “አስደናቂ ባህሪ ” ያለው ተጫዋች በሚል ኮከባቸውን አድንቀው “ባሎንዶርን ማሸነፍ ይገባዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

የ24 አመቱ ተጫዋች ባሳለፍነው የውድድር ዘመን ከክለቡ ጋር የላሊጋ እና ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ መቻሉን ተከትሎ ለታላቁ ግላዊ የተጫዋች ሽልማት ክብር ቅድሚያ ግምት የተሰጠው ተጫዋች ነው።

አምና ሁለተኛውን የሶክራትስ አዋርድን ማሸነፍ መቻሉም የሚታወስ ነው።ቪኒ በቻምፒየንስ ሊጉ ዶርትመንድ ላይ ያሳየው ብቃት አስገራሚ የሚባል ነው።

የባሎንዶር ክብሩ ተቀናቃኙ ማን ሊሆን ይችላል?

30 የመጨረሻ እጩ ተጫዋቾች ይፋ ሲደረጉ በዝርዝሩ ውስጥ ሀሪ ኬን ጁድ ቤሊንግሀም ፊል ፎደን ዴክላን ራይስ ቡካዮ ሳካ እና ኮል ፓልመር ከእንግሊዝ የተካተቱ ናቸው።

የቅርብ ተፎካካሪው እንደሚሆን የሚጠበቀው ግን የተከላካይ አማካዩ ሮድሪ ነው።

ከማንቺስተር ሲቲ ጋር የፕሪሚየር ሊጉን እና ከሀገሩ ስፔን ጋር ደግሞ የአውሮፓ ዋንጫውን ማሸነፍ ችሏል።

ቪኒ አምና በ51 ጨዋታዎች ሀያ ስድስት ጎሎችን አስቆጥሮ አስራ ሁለት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ለክለብ እና ሀገሩ አመቻችቶ አቀብሏል።

ከ2007 በኋላ ከሜሲ እና ሮናልዶ ውጭ ባሎንዶሩን ማሸነፍ የቻለ ሶስተኛው ተጫዋችም ይሆናል።

የቀድሞ ቡድን አጋሮቹ አሸናፊዎቹ ሉካ ሞድሪች በ2018 እና ካሪም ቤንዜማ በ2022 ናቸው።

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *