• Fri. Nov 20th, 2026

ለማድሪድ የሚጫወተው ብራዚላዊው Vinicius Junior በስፔን መጫወት ከጀመረ አንስቶ ፡ እስካሁን ድረስ ባሉት አመታት በሙሉ ፡ የተለያዩ የዘረኝነት ስድቦችን አስተናግዷል ።

Byadmin

Oct 25, 2024

ለማድሪድ የሚጫወተው ብራዚላዊው Vinicius Junior በስፔን መጫወት ከጀመረ አንስቶ ፡ እስካሁን ድረስ ባሉት አመታት በሙሉ ፡ የተለያዩ የዘረኝነት ስድቦችን አስተናግዷል ።

በዚህ ጥቃት ያልተበገረው ይህ ተጫዋች ግን ፡ የሚደርስበትን ፡ የዘረኝነት ጥቃት ችሎ እስካሁን አለ ።

…….

በዚህ ተጫዋች ላይ የሚደርስበትን ጥቃት የሚያወግዙ ብዙ ሰወች ከጎኑ ቢቆሙም ፡ በተቃራኒው የማይደግፉትም አሉ ።

ከነዚህ መሀከል ፡ ስፔናዊው ዩቲዩበር ኮኮ ዲሲ አንዱ አንዱ ነው ።

……..

በስፔን ውስጥ ታዋቂ የሆነውና ፡ ከ3 ሚሊየን በላይ ሰብስክራይበር ያለው ይህ ዩቲዩበር ፡ ስለ Vinicius ሲናገር ፡ ስፔን ውስጥ እንዲህ አይነት ጥቃት የለም ። ተጫዋቹ የዘረኝነት ሰለባ ሆኛለሁ እያለ እያጋነነ የሚያወራው ፡ ትኩረትን ለማግኘት ነው እያለ ይተቸዋል ።

………..

……….

ከቀናት በፊት ነው ……… ስፔን ውስጥ ዩቲዩበሮች ተሰባስበው የሚጫወቱበት ፡ አንድ የገቢ ማሰባሰቢያ ፡ የእግር ኳስ ጨዋታ ተዘጋጅቶ ነበር ።

…..

እና የስፔን ዩቲዩበሮችን ወክለው ከተሳተፉት ውስጥ ደግሞ ይህ Vinicius Junior ን በመተቸት የሚታወቀው ዩቲዩበር አንዱ ነበር ።

እና ጨዋታው ተጀምሮ እየተካሄደ እያለ ፡ ከስታዲየሙ የጦጣ ድምፅ መሰማት ጀመረ ።

ቀጥሎም ይህንን ዩቲዪበር የሚሰድቡ የዘረኝነት ስድቦች መሰማት ጀመሩ ። ዩቲዩበር ኮኮ በመጀመሪያ ደነገጠ ።

ከዛም ይህ ስድብ ይቆማል በሚል መጫወቱን ቀጠለ ፡ ሆኖም ልክ ኳስ እሱ እግር ስር ስትገባ ፡ ያ ስድብና ጩኸት ይቀጥላል ።

……….

በመጨረሻም. ….የዘረኝነት ጥቃት የለም እያለ Vinicius Junior ን የሚተቸው ዩቲዩበር ፡ እንደ ቪኒ እንኳን ለአመታት ፡ ለደቂቃም መታገስ አቅቶት ፡ ጨዋታውን አቋርጦ እያለቀሰ ከሜዳ ወጣ 😄 KARMA !

………..

ቪኒ የደረሰበትን ጉዳት ፡ አሁን በራሱ ሲደርስ አወቀው ።

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *