በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በተጫዋችነት እና በአሰልጣኝነት ለረጅም ጊዜ በማገልገል ግዙፍ አሻራቸውን ያሳረፉት አንጋፋው የእግር ኳስ ሰው አሥራት ኃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
አሥራት ኃይሌ በተጫዋችነት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ በጥጥ ማህበር እና በቅዱስ ጊዮርጊስ አገልግለዋል።
በአሰልጣኝነትም በተለያዩ ጊዜያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን እና የሀገሪቱን ክለቦች በመምራት የሴካፋ ድልን ጨምሮ የተለያዩ ስኬቶችን ማስመዝገብ የቻሉ ናቸው።
ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ የቆዩት አሥራት ኃይሌ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።