ጠንክረን ከሰራን ማንችስተር ዩናትድ ሊቆም የማይችል ቡድን ሊሆን ይችላል ሲል የቡድኑ ግዜያዊው አሰልጣኝ ሩድ ቫን ስቴልሮይ ተናገረ።
ዛሬ ምሽት በካራባኦ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ኦልትራፎርድ ላይ ማንችስተር ይናይትድ ሌስተር ሲቲን ሲያስተናግድ የቀድሞው የክለቡ አጥቂ ሩድ ቫኔስትሮይ ለመጀመሪያ ጊዜ አሰልጣኝ ሆኖ ይመራል፡፡
ከትናንት በስቲያ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግን ያሰናበተው ማንችስተር ዩናይትድ በግዚያዊ አሰልጣኙ ቫኒስትሮይ እየተመራ በፕሪምየር ሊጉ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ቫን ኒስቴልሮይ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት እ ኤ አ ከ2001 እስከ 2006 ባለው አመት በተጫዋችነት ለአምስት አመታት ያሳለፈ ሲሆን የፕሪሚየር ሊግ ፣ የኤፍኤ ካፕ እና የኤፍኤ ኮሚኒቲሺልድ ዋንጫን ማሸነፉ ይታወሳል፡፡
እንዲሁም ባለፈው ክረምት የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ረዳት ሆኖ ወደ ቡድኑ መመለሱ ይታወቃል፡፡
በክረምቱ የኤሪክ ረዳት ሆኜ ስመለስ ማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች ሆኜ ወደ ማውቀው ደረጃ ሊመለስ እንደሚችል ስለማምን ነበር የመጣሁት ሲል ቫን ኒስቴልሮይ ከሌስተር ጨዋታ በፊት ሀሳቡን ሰጥቷል፡፡
“አሁንም እንደዚያ እምነት አለኝ፤ግን ብዙ ጥረት ይጠይቃል፤በዚህ የውድድር አመት የቡድኑን አቅም አይተናል ነገር ግን በቂ እንዳልሆነ ግልጽ ነው” ብሏል፡፡
ይገደብ አባይ